በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“ፕሮፓጋንዳ” በሚዲያ ነፃነት ላይ ተፅእኖ የሚይሳድረው በምን መልኩ ነው?


“ፕሮፓጋንዳ” በሚዲያ ነፃነት ላይ ተፅእኖ የሚይሳድረው በምን መልኩ ነው?
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:40 0:00

“ፕሮፓጋንዳ” በሚዲያ ነፃነት ላይ ተፅእኖ የሚይሳድረው በምን መልኩ ነው?

ሩሲያ በዩክሬን ላይ የከፍተችው ጦርነት ሀሰተኛ መረጃዎች የሚፋለሙበት የውጊያ ሜዳ ከፍቷል። ለመሆኑ ፕሮፓጋንዳ በሚዲያ ነፃነት ላይ ተፅእኖ የሚይሳድረው በምን መልኩ ነው?

ድምበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን እንደ አውሮፓውያን የቀን አቆጣጠር በ2022 ዓ.ም ያወጣው የፕሬስ ነፃነት አመልካች ሪፖርት ለዚህ ምላሽ አለው ይለናል - ሲርዋን ካጆ ለአሜሪካ ድምፅ የላከው ዘገባ።

ፕሮፓጋንዳ፣ ተዓማኒነት ያላቸውን ሚዲያዎችን ማጣጣል፣ ድህረገፆችን ማገድ፣ እስሮች። - የሩሲያ ወታደሮች ዩክሬን መውረራቸውን ተከትሎ ሞስኮ በነፃው ፕሬስ ላይ የምታደርገው ጥቃት የበለጠ ተጠናክሯል።

በዚህ ምክንያት የሩሲያ የሚዲያ ነፃነት ደረጃ ወርዶ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2022 ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን ባወጣው የዓለም ፕሬስ ነፃነት ጠቋሚ ዝርዝር በመጨረሻ ደረጃ ወደተቀመጡ ሀገሮች ተርታ አውርዷታል።

ዓመታዊው የፕሬስ ነፃነት ጠቋሚ

"እጅግ በጣም የከፋ የሚዲያ ነፃነት" ብሎ ባስቀመጠው ምድብ ዘንድሮ 28 ሀገራት በመግባታቸው ከፍተኛ ቁጥር ሆኖ ተመዝግቧል። እነዚህ ሀገራት የተቀላቀሉት ቅድመ ምርመራ የምታስፋፋውና የክሬምሊንን ፕሮፓጋንዳ የምታስተጋባው ቻይናን የመሳሰሉ ሀገራት ነው።

በቤይጂንግ ተፅእኖ፣ ሚዲያዎች ላይ ከበባ በማድረግና ጋዜጠኞችን በማሰር የዲሞክራሲ ተሟጋች የሆኑ የዜና ድረገፆች እንዲዘጉ ባደረገችው ሆንግ ኮንግም የፕሬስ ነፃነት ወርዶ ከ180 ሀገራት 148ኛ ደረጃ ላይ እንድትቀመጥ አድርጓታል።

በኢትዮጵያ እና ኒካራጉዋም እንዲሁ ባለሥልጣናት በሚዲያ ላይ በሚያደርጉት አፈና፣ ቅድመ ምርመራ እና የማገድ ተግባር ከነበሩበት ደረጃ በከፍተኛ ሁኔታ አሽቆልቁለዋል።

ድምበር የለሹ የጋዜጠኞች ቡድን እንደሚለው ከሁሉ እጅግ አሳሳቢው የሚዲያዎች ፅንፈኝነት እና የሐሰተኛ መረጃዎች ሥርጭት በማኅበረሰቡ ላይ እያሳደረ ያለው ተፅእኖ ነው።

በዩናይትድ ስቴትስ የሚገኘው የድንበር የለሽ ጋዜጠኞች ቡድን ምክትል ዳይሬከተር የሆኑት ክሌይተን ዊመርስ ስለሁኔታው ሲያስረዱ "እንደ አውሮፓውያን የቀን አቆጣጠር በ2022 የሚዲያ ፅንፈኝነት እና የተደበላለቀ መረጃ በማኅበረሰቡ ዘንድ ታይቶ የማይታወቅ ክፍፍልን እያባባሰ መሆኑ የማይካድ ሀቅ ነው።" ብለዋል።

ሥልጣን ለመጨበጥ የሚደረግ ሽኩቻም በሚዲያው ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ ያሳደረ ሲሆን በአንዳንድ ቦታዎች በዓመታት ውስጥ የታዩ መሻሻሎችን ሙሉ ለሙሉ አውድሟቸዋል።

ለምሳሌ በማይናማር የተደረገው መፈንቅለ መንግስት የሚዲያ መብቶችን አስር ዓመት ወደ ኃላ መልሷቸዋል። ጋዜጠኞች ታስረዋል፣ የሚዲያዎች ፈቃድ ተነጥቋል፣ በርካታ የዜና ማሰራጫ ተቋማት ተመልሰው ወደ ውጪ ሀገራት እንዲሰደዱ ተደርገዋል።

በአፍጋኒስታንም ታሊባን የፕሬስ ነፃነትን ለማስቀጠል ቃል ገብቶ የነበረ ቢሆንም በተቃራኒው የጋዜጠኞችን መብት የሚገድቡ ህጎችን በማውጣት ሴት ጋዜጠኞች አየር ላይ እንዳይወጡ አግዷል። በመዝናኛ ዝግጅቶች እና ማስታወቂያዎች ላይ ገደብ በመጣሉም የሚዲያ ተቋማት የገንዘብ ችግር ውስጥ እንዲገቡ አድርጓቸዋል።

ኢትዮጵያ ውስጥም በትግራይ ክልል በተካሄደው ጦርነት የግንኙነት መስመሮች እንዲቋረጡ እና መረጃ ማግኘት እንዳይቻል በመደረጉ ሀገሪቱ ቀደም ሲል ከነበራት ደረጃ በ 13 ነጥብ ዝቅ ብላ 114ኛደረጃ ላይ እንድትቀመጥ አድርጓታል። ከሶስት አመት በፊት በሀገሪቱ በተደረጉ ለውጦች ከፍተኛ አድናቆትን አግኝታ ለነበረችው ሀገር ይህ አሳዛኝ ውጤት ነው።

ይህ አይነቱ ማሽቆልቆል እና አምባገነኖች የሚጠቀሙባቸው ስልቶች እየተስፋፉ መሄዳቸውን የድምበር የለሹ ጋዜጤኞች ቡድን ምክትል ዳይሬክተር ያስረዳሉ።

"በአምባገነን መንግሥታት መካከል የሚተላለፍ ነገር አለ። ባለሥልጣናት እንደፈለጉ ጋዜጠኞችን እያሳደዱ፣ እያስጨነቁ፣ እያሰሩ፣ በየመንገዱ እየደበደቡ እና እየገደሉ ተጠያቂነት እንዳይኖር የሚያደርግ አሰራርን ስንፈቅድ ተዘዋዋሪ ተፅእኖ ይኖረዋል። አምባገነኑ ደግሞ ያንኑ ደግሞ እንዲፈፅም የልብ ልብ ይሰጠዋል፣ ሌላው ያንን የሚመለከት አምባገነንም ተመሳሳይ ነገር እንዲፈፅም ያበረታታዋል።” በማለት ያስረዳሉ።

ዩናይትድ ስቴትስ እ.አ.አ በ2021 ከነበረበችበት ደረጃ በተወሰነ ደረጃ መሻሻል ብታሳይም ጋዜጠኞች እና የሚዲያ ተቋማት ግን የተለያዩ ክፍለግዛቶችን መንግስታትና ተቃውሞዎችን ጨምሮ ዘገባዎችን ለመስራት አሁንም እንቅፋቶች እንዳሉባቸው ይገልፃሉ።

የብሄራዊ ፕሬስ ክለብ የጋዜጠኝነት ተቋም ባልደረባ የሆኑት ቤት ፍራንሲስኮ ስለጉዳዩ ሲያስረዱ፤

"ይሄ የሚሆንበት ምክንያት ወይ ለህዝብ ክፍት የሆኑ ሰነዶችን እና ስብሰባዎችን አስመልክቶ ያለውን ህግ ግልፅ በሆነ መልኩ አለማክበር ነው ወይም ደግሞ በተሳሳተ መንገድ ትርጉም እየሰጧቸው ነው። አንድ ግለሰብ ጋዜጠኛ በአንድ ስነስርዓት ላይ መገኘት መቻል ወይም አለመቻሉን በተሳሳተ መንገድ እየተረጎመው ነው።" ብለዋል።

የፕሬስ ነፃነትን ለመጠበቅ ዲሞክራሲ ትልቁን ሚና ይጫወጣል። ሆኖም የሀሰተኛ መረጃ እና ፕሮፓጋንዳ እያጨመረ መሄድ በገለልተኛ ሁኔታ የሚሰሩ ዜናዎች ላይ አደገኛ የሆነ ተፅእኖ እያሳደረ መሆኑን የድምበር የለሹ ጋዜጠኞች ቡድን ግኝት አመልክቷል።

XS
SM
MD
LG