በአሜሪካ ዛሬ የፕሬዝደንቶች ቀን ነው። ዕለቱ የመጀመሪያው የአሜሪካ ፕሬዝደንት የልደት ቀን ተደርጎ እንዲከበር በአሜሪካ ም/ቤት ከተደነገጉት 11 በዓላት አንዱ ነው። የፕሬዝደንቶች ቀን ይባል እንጂ፣ ም/ቤቱ ዕለቱን የሰየመው ‘የዋሽንግተን የልደት ቀን’ በሚል ነው።
እንደ ሌሎቹ የአሜሪካ መሥራች አባቶች ሁሉ ጆርጅ ዋሽንግተን በሃገር ደረጃ ክብር እንዲሰጣቸው የሚሹ ዓይነት ሰው እንዳልነበሩ የታሪክ አዋቂዎች ይናገራሉ።
የመንግሥት ሥራ እና ባንኮች ዛሬ ዝግ ናቸው። በመኾኑም በዕለቱ ሰዎች ጊዜ ስለሚኖራቸው ወደ ገበያ የሚያቀኑበት ቀን ስለሆነ የታሪክ አዋቂዎች ቀኑ ትርጉሙ አጥቷል የሚል ቅሬታ ያሰማሉ።
ዋሽንግተን በፕሬዝደንትነት በቆዩባቸው በአብዛኛው ዓመታት አቻዎቻቸው ልደታቸውን ያከብሩላቸው ነበር። ነገር ግን የመጀመሪያው ፕሬዝደንት መሆናቸው ከእንግሊዝ ዘውዳዊ አገዛዝ አንጻር ያለውን ልዩነትና አንድምታ ስለሚያውቁ እንደ ንጉሥ እንዲከበሩ ይፈልጉ እንዳልነበር የታሪክ አዋቂዎች ይናገራሉ።
መድረክ / ፎረም