በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፕሬዚደንት ትራምፕ እና የ2015 የኢራን የኑክሊየር ስምምነት ጉዳይ


ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ እአአ በ2015 ከኢራን ጋር የተደረሰውን የኑክሊየር ስምምነት እንደማይቀበሉ በቀጣዮቹ ቀናት ውስጥ ይፋ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ እአአ በ2015 ከኢራን ጋር የተደረሰውን የኑክሊየር ስምምነት እንደማይቀበሉ በቀጣዮቹ ቀናት ውስጥ ይፋ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል። ለዚህ ውሳኔያቸውም ለምክር ቤቱ የ60 ቀናት የጊዜ ገደብ በመስጠት ቴህራን ላይ የተጣለው የዩናይትድ ስቴትስ ማዕቀብ ስለሚቀጥልበት ሁናቴ ከውሳኔ ይደረሳል ተብሏል።

ፕሬዚደንቱ ይህን ጉዳይ በሚቀጥሉት አራት ቀናት ውስጥ መወሰን እንዳለባቸው ህጉ ይጠይቃል፤ ዋይት ኃውስ ግን፣ ቀደም ብሎ ሊወሰን እንሰሚችልም አመልክቷል።

ፕሬዚደንቱ ኢራን አስመልክቶ ከአንድ አጠቃላይ ውሳኔ ላይ እንደደረሱ የዋይት ኃውስ ቃል አቀባይ ሳራ ሃከቤ ሳንደርስ አመልክተው፣ “ኢራን መጥፎ ተዋናይ መሆኗን ግንዛቤ ላይ ደርሰዋል” ሲሉ ገልፀዋል።

ፕሬዚደንት ትራምፕ ባለፈው ወር በተካሄደው የተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ፣

“ከኢራን ጋር የተደረሰው የኑክሊየር ጦር መሳሪያ ስምምነት፣ ለዩናይትድ ስቴትስ ትልቅ ማፈሪያ ብቻ ሳይሆን፣ ወደ አንድ ወገን ያጋደለ ኢ-ፍትሃዊም ነው” ማለታቸው አይረሳም።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG