በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፕሬዚደንት ትረምፕ ነገ ከሆስፒታል ሊወጡ ይችላሉ ተብሏል


ፕሬዚደንቱ ትረምፕ እየታከሙ ከሚገኙበት ከዎልተር ሪድ ወታደራዊ ሆስፒታል ቢሮ ውስጥ ተቀምጠው
ፕሬዚደንቱ ትረምፕ እየታከሙ ከሚገኙበት ከዎልተር ሪድ ወታደራዊ ሆስፒታል ቢሮ ውስጥ ተቀምጠው

በኮቪድ - 19 ምክንያት ሆስፒታል የገቡት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ትረምፕ የደማቸው የኦክሲጂን መጠን ሁለቴ ለአጭር ጊዜ ወርዶ እንደነበረ ፕሬዚደንቱን እያከሙ ያሉት ዶክተሮች ዛሬ ተናገሩ።   

የፕሬዚደንቱ ዋናው ሃኪማቸው ዶክተር ሻን ኮንሊ "እንደዕውነቱ ከሆነ በጣም በጎ ናቸው" ብለዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ ባህር ሃይል አዛዥነት ማዕረግም ባላቸው ዶክተር ሻን ኮንሊ የሚመሩት ሃኪሞች ከኋዋይት ሃውስ ሪፖርተሮች ብዙ ጥያቄዎች ከቀረቡባቸው ካለፉት ጋዜጣዊ መግለጫዎች በተሻለ ግልጽ መረጃ ሰጥተዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ ባህር ሃይል አዛዥነት ማዕረግም ባላቸው ዶክተር ሻን ኮንሊ የሚመሩት ሃኪሞች
የዩናይትድ ስቴትስ ባህር ሃይል አዛዥነት ማዕረግም ባላቸው ዶክተር ሻን ኮንሊ የሚመሩት ሃኪሞች

ፕሬዚደንቱ ዓርብ ዕለት ዋይት ሃውስ እያሉ ተጨማሪ የኦክሲጂን ዕገዛ አስፈልጉዋቸው እንደነበር፥ ለአንድ ሰዓት ያህል የኦክሲጂን ድጋፉ አስፈልጎ ነበርና ለምን ደበቁ ተብለው በጋዜጠኛ የተጠየቁት ዶክተር ኮንሊ"የህክምና ቡድናችንን ተስፋ የሰነቀ አመለካከት ለማንጸባረቅ መሞክሬ ነበር፥ እኛ መረጃውን ብንሰጥ የህመማቸውን ሁኔታ ወደሌላ አቅጣጫ ይወስደዋል በሚል እንጂ ለመደበቅ ከመፈለግ አይደለም" ሲሉ አስረድተዋል።

ዶክተሮቹ ፕሬዚደንቱ እየታከሙ ከሚገኙበት ከዎልተር ሪድ ወታደራዊ ሆስፒታል በራፍ በሰጡት በዛሬው ጋዜጣዊ መግለጫ ስቴሮይድ፥ ዴክሳሜታዞንና ለአምስት ቀናት የሚወሰደው ጸረ ቫይረስ መድሃኒት ሬምዴዚቪር እየተሰጣቸው መሆኑን ገልጸዋል ። ዴክሳሜታዞን በጣም ላልታመሙ የኮቪድ ህሙማን በተለምዶው የሚሰጥ አይደለም።

የሳምባ ጨምሮ የመተንፈሻ አካላት አጠቃላይ ጤና ሃኪም የሆኑት የጦር ሰራዊቱ ኮሎኔል ዶክተር ሻን ዱድሊ በበኩላቸው የዛሬ ጠዋት የፕሬዚደንቱ የጤና ይዞታ ምልክቶች( የደም ግፊት፥ የልብ ምት ፥ የሰውንት ሙቀት እና አተነፋፈስ) በደህና ሁኔታ ላይ እንዳሉ ገልጸዋል። ወዲያ ወዲህ ይራመዳሉ ፥ የትንፋሽ ማጠርም ይሰማኛል አላሉም ፥ ሌላ የመተንፈሻ አካላት ችግር አልታየባቸውም ሲሉ አብራርተዋል።

የጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲው የህክምና ትምህርት ቤት የመተንፈሻ አካላት ልዩ ሃኪምና የአጣዳፊህክምና ክትትል ልዩ ሃኪሙ ዶክተር ብራያን ጋሪባልዲ በበኩላቸው " እንደዛሬ ይዞታቸው ከቀጠሉና ደህንንት ከተሰማቸው ነገም ቢሆን ከሃኪም ቤቱ ወጥተው ሁዋይት ሃውስ ሆነው ህክምናቸውን የሚቀጥሉበትን ዕቅድ ማዘጋጀት እንችላለን ብለን ተስፋ እናደርጋለን" ብለዋል።


ያም ሆኖ አንዳንድ ቁልፍ የሆኑ ያልተመለሱ ጥያቄዎች አሉ ፥ፕሬዚደንቱ ሳንባቸው ተጎድቱዋል ወይ? የሚለው አንዱ ነው፤ ፕሬዚደንቱ ሰባ አራት ዓመታቸው ነው፥ ከሚገባው በላይ የሰውነት ክብደት ያላቸውና ሲጋራም የማያጨሱ ሲሆኑ ሃኪሞቻቸው በዛሬው መግለጫቸው ታካሚያቸው ላይ " የሚጠበቁ ነገሮች" ከማለት አልፈው ሊያብራሩ አልፈለጉም።

ፕሬዚደንት ትረምፕና ቀዳማዊት ዕመቤት ሚላንያ በምርመራ ኮሮና ቫይረስ እንደያዛቸው ሃሙስ ማታ የታወቀው የፕሬዚደንቱ የቅርብ ረዳት የሆኑት ሆፕ ሂክስ ቫይረሱ ይዙዋቸው መታመማቸውን ተከትሎ ነው።


የዋይት ሃውስ የብሄራዊ ጸጥታ አማካሪ ሮበርት ኦብራያን ዛሬ በሰጡት ቃል "ፕሬዚደንታዊ ስልጣኑን በጊዜያዊነት ወደ ምክትል ፕሬዚደንት ማይክ ፔንስ የማዛወር ጉዳይ አልተነሳም ፤ አስተዳደሩ በደምብ እየሰራ ነው፤ ለሁሉም ጉዳይ ዕቅድ ስላለን" ብለዋል።

ፕሬዚደንት ትረምፕ ትናንት በትዊተር ገጻቸው በባስተላለፉት የቪዲዮ መልዕክት "በጣም በጎ ነኝ ፥ ቶሎ እወጣለሁ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፥ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት የሚሆነው ይታወቃል" ብለዋል።

XS
SM
MD
LG