የኢትዮጵያ መንግሥት እና ተቋማት፣ በሐማስ የተፈጸመውን ጥቃት እንዲያወግዙ፣ በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አለልኝ አድማሱ በሰጡት መግለጫ ጠይቀዋል፡፡
የኢትዮጵያ መንግሥት እስከ አሁን ስለጥቃቱም ይኹን ስለ ግጭቱ በይፋ የሰጠው መግለጫ የለም፡፡
ኾኖም፣ ኢትዮጵያ ገለልተኛ አቋም እንዳላትና ግጭቱ በሰላም እንዲፈታ እንደምትፈልግ፣ በእስራኤል የኢትዮጵያ አምባሳደር፣ ትላንት ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡
የሐማስ ጥቃት በተፈጸመበት ወቅት፣ በእስራኤል እንደነበሩ የተናገሩ አንድ የኤምባሲው ባልደረባ፣ በወቅቱ በሕዝቡ ዘንድ ስለነበረው መረበሽ አብራርተዋል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም