በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሱዳንን ከኤርትራ የሚዋሰነው ድንበር ሊከፈት ነው


ፎቶ ፋይል፡- የሱዳን ፕሬዚዳንት ኦማር ሃሰን አል-ባሺር
ፎቶ ፋይል፡- የሱዳን ፕሬዚዳንት ኦማር ሃሰን አል-ባሺር

የሱዳን ፕሬዚዳንት ኦማር ሃሰን አል-ባሺር ለአንድ ዓመት ያህል ተዘግቶ የቆየው ከኤርትራ ጋር የሚዋሰነው ድንበር እንደሚከፈት ዛሬ አስታውቀዋል።

የሱዳን ፕሬዚዳንት ኦማር ሃሰን አል-ባሺር ለአንድ ዓመት ያህል ተዘግቶ የቆየው ከኤርትራ ጋር የሚዋሰነው ድንበር እንደሚከፈት ዛሬ አስታውቀዋል።

ሱዳን ባለፈው ዓመት ጥር ወር ላይ ድንበሩን የዘጋችው የመሳርያና የምግብ ህገ ወጥ ዝውውርን ለመግታት በሚል በከሰላና በሰሜን ኮርዱፋን ክልሎች የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ካወጀች በኋላ ነበር።

“እዚህ ከሰላ ላይ ሆኜ ከኤርትራ ጋር የሚዋሰነው ድንበር እንደሚከፈት አስታውቃለሁ። ምክንያቱም ወንድሞቻችንና ህዝባችን ናቸውና። ፖለቲካ ሊለያየን አይገባም” ሲሉ በቴሌቪዥን በተላለፈ ንግግር አስታውቀዋል።

አል-ባሺር ከሰላ ላይ ንግግር ባደረጉበት ወቅት በአገዛዛቸው ላይ ተቃውሞ እንዲነሳ ጥሪ የሚያደርገው የሱዳን ባለሙያዎች ማኅበር ዛሬ በብዙ የሱዳን ከተማዎች የተቃውሞ ሰልፍ እንዲካሄድ ቀስቅሷል።

ሱዳን ካለፈው ነሃሴ ወር አንስቶ ከሞላ ጎዳል በየቀኑ በተቃውሞ ስትናጥ ቆይታለች። በተከተለው ግጭት ቢያንስ 45 ሰዎች መገደላቸውን የሰብዓዊ መብት ቡድኖች ገልጸዋል። መንግሥት ግን የሞቱት 30 ናቸው ይላል። አል ባሺር በበኩልቸው ስለተቃውሞው ከሰላ ላይ ባደረጉት ንግግር “ፕሬዚዳንትን የመለወጡ ጉዳይ በፌስ ቡክና በዋትስአፕ በኩል ሳይሆን በምርጫ ሳጥን ነው” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። “በሀገሪቱ ህዝብ ፊት ቆመን የምንሰጠው ቃልና ቁርጠኝነት ይህ ነው። ሰፊው የሱዳን ህዝብ ውሳኔው ያንተ ነው” ሲሉም አስገንዝበዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG