ዋሺንግተን - ዲ.ሲ —
የፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማን ንግግር በቪድዮ ለማየት ከታች የተቀመጠውን የዋይት ሃውስ ዌብ ሣይት ማገናኛ ይጫኑና ይከተሉ
http://www.whitehouse.gov/blog/2014/05/28/america-must-always-lead-president-obama-addresses-west-point-graduates
የፕሬዚዳንት ባራክ ኦባን ንግግር ሙሉ ቃል በፅሁፍ /በእንግሊዝኛ/ ለማግኘት ከታች የተመለከተውን ማገናኛ ይጫኑና ይከተሉ
http://www.whitehouse.gov/the-press-office/remarks-president-address-nation-way-forward-afghanistan-and-pakistan
ዩናይትድ ስቴትስ በዓለም መተኪያ የሌላት ሃገር ሆና ትቀጥላለች አሜሪካ እራሷን ከሌሎች ነጥላ የማቆሟ ሃሣብ የሚፈለግ አማራጭ አይደለም፤ ለያንዳንዱ ችግርም ወታደራዊ መንገድ መፍትሔ አይደለም ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ዛሬ ለካዴቶች ባደረጉት የመመረቂያ ንግግር ላይ ተናግረዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ ዌስት ፖይንት በሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ወታደራዊ አካዳሚ ተገኝተው የአስተዳደራቸው ዘመን ቀሪ ጊዜ የአሜሪካ የውጭ ፖሊሲ አብይ አቅጣጫ የተባለ ንግግር ነው ያደረጉት፡፡
“ሽብር ለአሜሪካ ቀጥተኛ ሥጋቷ ነው” ያሉት ፕሬዚዳንት ኦባማ ይሁን እንጂ ሽብር ፈጠራን የምንዋጋበትን አያያዝ መቀየር፣ የሽብር ፈጠራ መረቦች ሥር ከሰደዱባቸው ሃገሮች ጋር የአጋርነት ሥራዎችን ማከናወን የተሻለው አማራጭ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
“ዩናይትድ ስቴትስ ሕዝቧንና ግዛቷን ከአደጋ ለመጠበቅ ማንንም ፍቃድ አትጠይቅም” ብለዋል ኦባማ፡፡ ይሁን እንጂ ለአሜሪካ ቀጥተኛ ሥጋት የማይፈጥሩ ዓለምአቀፍ ችግሮች ሲፈጠሩ ወደ ወታደራዊ መንገድ የመሄዱ ውሣኔ ብዙ መታቀብን የሚፈልግ መሆኑን አመልክተዋል፡፡
የሽብር ፈጠራ ችግር ያለባቸውን ሃገሮች በሥልጠና በቅኝትና በስለላ፣ ልዩ ዘመቻዎችን እንዲያካሂዱ በማስቻል በኩል አቅማቸውን ለማጠናከር የሚውል የ5 ቢሊየን ዶላር በጀት እንደሚያስፈቅዱ ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል፡፡
አቻ ወይም መሰል የሌለው ሲሉ የጦራቸውን ጥንካሬ አጉልተው የተናገሩት ፕሬዚዳንት ኦባማ አሜሪካ የጦር ኃይሏን ጣልቃ ካላስገባች ደከመች ማለት ነው ከሚል የተቺዎች አስተያየትና አስተሳሰብ መራቅ አለብን ብለዋል፡፡
“አሜሪካ በዓለምአቀፍ መድረክ ላይ ሁልጊዜ መሪ መሆን አለባት፡፡ እኛ ካልመራን ሌላ ማንም ሊመራ አይችልም፡፡ አሁን የገባችሁበት ጦር የዚያ አመራር የጀርባ አጥንት ነው፤ ወደፊትም እንደዚሁ ሆኖ ይቀጥላል፡፡ ይሁን እንጂ የዩናይትድ ስቴትስ ወታደራዊ እርምጃ በየመስኩ ለምንሰጠው አመራር ብቸኛው አማራጭ፤ እንዲያውም በቅድሚያ የሚታይም ሊሆን አይችልም፡፡ ምንም እንኳ በዓለም እጅግ ምርጥ ወይም ጠንካራ የሆነ መዶሻ ቢኖረንም እያንዳንዱ ችግር ሚስማር ነው ብለን ማሰብ የለብንም፡፡ ከወታደራዊ እርምጃዎች ጋር የተያያዙት ወጭዎች እጅግ ከፍተኛ በመሆናቸው ማንኛውም ሲቪል መሪ በተለይ ደግሞ ጠቅላይ አዛዣችሁ ይህንን ታላቅ ኃይል እንዴት እንደሚጠቀሙበት ግልፅ እንዲደደርጉላችሁ መጠበቅ ይኖርባችኋል፡፡” ብለዋል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ በአሜሪካ ጥንካሬ ምክንያት ዛሬ በብዙ የዓለም ሃገሮች በሕዝብ የተመረጡ መንግሥታት ሥልጣን መያዛቸውን ፕሬዚዳንቱ ተናግረው “የአሜሪካ ጥንካሬ የሚመነጨው በተፅዕኖ ከመምራት ሳይሆን በአርአያነት በመምራት ነው” ብለዋል፡፡
“እንደ ሌሎች ሃገሮች ሳንሆን እኛ የግለሰቦች አቅምና ውሣኔ ሰጭነት አቅምን መጠናከር አንፈራም፡፡ እንዲያውም የምንጠነክረው በእርሱ ነው፡፡ እኛ የምንጠነክረው በሲቪል ማኅበረሰቦች ነው፡፡…
“… የምንጠነክረው በነፃ ፕሬስ ነው፡፡ የምንጠነክረው እየታገሉ ባሉ ሥራ ፈጣሪዎችና አነስተኛ ንግዶች ነው፡፡ የምንጠነክረው ለሁሉም ሰዎች ለልጃገረዶች፣ ለሴቶችም በትምህርት ልውውጥና በዕድሎች መስፋትም ነው፡፡ እንዲህ ነን እኛ፤ የምንወክለውም ይህንን ነው” ብለዋል ፕሬዚዳንቱ፡፡
ባለፈው ዓመት አፍሪካን ጎብኝተው በነበረ ጊዜ ይህ ምን ያህል እውነት እንደሆነ ማየታቸውን ገልፀዋል፡፡
“በዚያ የአሜሪካ ድጋፍ ከኤድስ ነፃ የሆነን ትውልድ የመፍጠርን ትልም ዕውን አድርጓል፡፡ አፍሪካዊያን ሕሙማኖቻቸውን መንከባከብ እንዲችሉ እያገዝናቸው ነው፡፡ በአንድ ወቅት ለረሃብ ቸነፈር አደጋ የተጋለጡ ቤተሰቦች ምግብ እንዲያገኙ፣ ገበሬዎች ምርቶቸቸውን ወደ ገበያ እንዲያወጡ እያገዝን ነው፡፡ አፍሪካዊያን በዓለምአቀፉ ምጣኔ ኃብት ውስጥ ተሣታፊ እንዲሆኑ ለማስቻል ከሰሃራ በስተደቡብ ባለው አፍሪካ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት በእጥፍ እንዲያድግ አስችለናል፡፡” ብለዋል፡፡
በዚም - አሉ ኦባማ - አዳዲስ አጋሮችን እየፈጠርን ሽብርተኝነትና ግጭቶች ቦታ እንዳይኖራቸው ማድረግ እንችላለን፡፡
ናይጀሪያ ውስጥ ልጃገረድ ተማሪዎችን የጠለፈው ፅንፈኛ ቡድን ቦኮ ሃራም የፈጠረውን ሥጋት ለማጥፋት እንሠራለን ያሉት ኦባማ ከዚያም ባሻገር ሄደን የናይጀሪያ መንግሥት ወጣቶቹን ማስተማር እንዲችል እናግዛለን ብለዋል፡፡
ሕፃናት ከትምህርት ቤት የማይጠለፉባት፣ ሰዎች በእምነታቸው ምክንያት የማይገደሉባት ዓለም እንድትመጣም ፕሬዚዳንቱ መሻታቸውን ተናግረዋል፡፡
ለዘገባውና ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ላደረጉት ንግግር ሙሉ ቃል /በእንግሊዝኛ/ የተያያዙትን የድምፅ ፋይሎች ያዳምጡ፡፡