በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቡሩንዲያዊያን ለሰላም እንዲቆሙ ኦባማ ጥሪ አሰሙ


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ /ፎቶ - ፋይል/
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ /ፎቶ - ፋይል/

ቡሩንዲያዊያን ወደ ፀብ ከሚወስዱ መንገዶች እንዲቆጠቡና ሰላም ለማውረድ እንዲመክሩ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ አሳሰቡ፡፡

ጭር ያለች ቡጁምቡራ
ጭር ያለች ቡጁምቡራ

ቡሩንዲያዊያን ለሰላም እንዲቆሙ ኦባማ ጥሪ አሰሙ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:03 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ቡሩንዲያዊያን ወደ ፀብ ከሚወስዱ መንገዶች እንዲቆጠቡና ሰላም ለማውረድ እንዲመክሩ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ አሳሰቡ፡፡

ፕሬዚዳንቱ ትናንት ለቡሩንዲያዊያን በቀጥታ ባደረጉት ንግግር ለሰላም በሚደረገው ጥረት ውስጥ ዩናይትድ ስቴትስ ከጎናቸው እንደምትቆም ተናግረዋል፡፡

ቡሩንዲ ኩሩና ቆንጆ ሃገር መሆኗን በማወደስ መልዕክታቸውን የጀመሩት ፕሬዚዳንት ኦባማ “… ከቅርብ ወራት ወዲህ ግን የምትወድዷት ሃገራችሁ ዕጣ ፈንታ ለአደጋ እንዲጋለጥ ተደርጓል” ብለዋል፡፡

መሪዎቻቸው የጥላቻና የዘለፋ ንግግሮችን እየተለዋወጡ መሆናቸውን፣ አሳሳቢ የሆኑ ሁከቶች ሕፃናትና ሴቶችን ጨምሮ የብዙ ሰዎችን ሕይወት መቅጠፋቸውን ገልፀው ከቡሩንዲ ያለፈ ታሪክ እንዲህ ዓይነቱ ሁከት ወደየት ሊያመራ እንደሚችል በማስታወስ አስጠንቅቀዋል፡፡

ይሁን እንጂ ቡሩንዲያዊያን ዛሬ የተለየ መንገድ መምረጥ እንደሚችሉ ጠቁመዋል ኦባማ፡፡

ለሰላም በሚያደርጉት መንገዱ ላይም የቡሩንዲ ሕዝብ ብቻውን እንዳልሆነ፣ ለብዙ ዓመታት በአካባቢው ያሉ ሃገሮችና ዩናይትድ ስቴትስ ቡሩንዲያዊያን ሰላማዊና ይበልጥ የጠነከረች ሃገር እንዲመሠርቱ ሲያግዙ መቆየታቸውን አስታውሰዋል፡፡

“አሁን የማናግራችሁ እንደ አጋርና እንደ ጓደኛ ነው …” ያሉት ሚስተር ኦባማ የቡሩንዲ መሪዎች የጥላቻና የመለያየት ቋንቋን እንዲያቆሙ፣ ከቡሩንዲ ዋጭ በሚደረግ ዓለምአቀፍ አደራዳሪዎች በሚጠሯቸው ድርድሮች ላይ ለመሣተፍ ባላቸው ቁርጠኝነት እንዲገፉ አሳስበዋል፡፡

የቡሩንዲ ወታደሮች ዋና ከተማይቱ ቡጁምቡራ ውስጥ ወደ ሰማይ እየተኮሱ የተቃውሞ ሰልፍ ሲበትኑ
የቡሩንዲ ወታደሮች ዋና ከተማይቱ ቡጁምቡራ ውስጥ ወደ ሰማይ እየተኮሱ የተቃውሞ ሰልፍ ሲበትኑ

ለቡሩንዲ ጦርም ባስተላለፉት መልዕክት “እናንተ ያላችሁት የቡሩንዲን መከፋፈል ለማስቀረትና ሃገሪቱን ወደ አንድነት ለመውሰድ ነው፡፡ እናንተ የቡሩንዲ ወንድና ሴት ልጆች ናችሁ፡፡ በመላ አፍሪካ ተሠማርታችሁ ሰላምን ለማስከበር አግዛችኋል፡፡ አሁን ደግሞ እራሣችሁን ከፖለቲካ ግጭቶች ውጭ አድርጋችሁ የቡሩንዲን ሕዝብ ደኅንነት በመጠበቅ የራሣችሁን ሃገር ልታግዙ ይገባል” ሲሉ መክረዋል፡፡

ለመላ ቡሩንዲያዊያንም - አሉ ኦባማ “… አብራችሁ ስትቆሙ ምን ልትሠሩ እንደምትችሉ አስታውሱ፡፡ ከቅኝ ግዛት እንዴት እንደወጣችሁ፣ አዲስ ሃገር እንዴት እንደገነባችሁ አስታውሱ፡፡”

ከእርስ በርሱ ጦርነት በኋላም የተሻለች ሃገር ለመገንባት ቡሩንዲያዊያን ያደረጉትን መረባረብ አንስተው “የፖለቲካ ትንቅንቅና የጥላቻ ድምፆች እነዚያን ጥንካሬዎች እንዳይነጥቋችሁ” ሲሉ አሳስበዋል፡፡

“ዕጣ ፈንታችሁ፤ እነሆ በእጃችሁ ይገኛል” ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ለቡሩንዲ ሕዝብ ትናንት ምሽት ላይ በቀጥታ ባስተላለፉት መልዕክት፡፡

XS
SM
MD
LG