በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን በማርቲን ሉተር ኪንግ ቤተ ክርስቲያን ንግግር አደረጉ


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የማርቲን ሉተር ኪንግን ልደት በዓል ምክንያት በማድረግ ንግግር ሲያደርጉ፤ ጆርጂያ፣ አትላንታ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የማርቲን ሉተር ኪንግን ልደት በዓል ምክንያት በማድረግ ንግግር ሲያደርጉ፤ ጆርጂያ፣ አትላንታ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የማርቲን ሉተር ኪንግን ልደት በዓል ምክንያት በማድረግ ትናንት ዕሁድ በሲቪል መብቶች መሪው አቤነዘር ባፕቲስት ቤተ ክርስቲያን ተገኝተው ንግግር አደረጉ።

ጆርጂያ ክፍለ ሀገር አትላንታ ከተማ የሚገኘውን ቤተ ክርስቲያን ""የአሜሪካ ነጻነት ቤተ ክርስቲያን" ሲሉ የገለጹት ባይደን "ዲሞክራሲ አደጋ ላይ ነው፣ የሲቪል መብቶች መሪው ህይወት እና ታሪካዊ ቅርስ ልንከተለው የሚገባንን መንገድ ያሳየናል እና ከልባችን ማድመጥ አለብን" ብለዋል።

ባይደን በሲቪል መብቶች መሪው ቤተ ክርስቲያን ለምዕመናን ስብከት ያሰሙ የመጀመሪያው በሥልጣን ላይ ያሉ ፕሬዚዳንት ናቸው።

ኪንግ ባንድ ወቅት "ከቶ ከእንግዲህ ወዴት ይሆን የምናመራው?" ሲሉ ለአሜሪካ ህዝብ ጥያቄ አቅርበው እንደነበር የጠቀሱት ባይደን እኔም በሲቪል መብቶች መሪው ልደት "አምባገነንነትን ሳይሆን ዲሞክራሲን መርጠናል የሚለውን መልዕክቴን አስተላልፋለሁ"ብለዋል።

XS
SM
MD
LG