በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፕሬዚደንት ኢሳይያስ አፈወርቂ እና የሩሲያ ፕሬዚደንት ፑቲን ተወያዩ


የሩሲያ ፕሬዚደንት ቭላዲሚር ፑቲን የኤርትራ ፕሬዚደንት ኢሳይያስ አፈወርቂ
የሩሲያ ፕሬዚደንት ቭላዲሚር ፑቲን የኤርትራ ፕሬዚደንት ኢሳይያስ አፈወርቂ

የሩሲያ ፕሬዚደንት ቭላዲሚር ፑቲን የኤርትራ ፕሬዚደንት ኢሳይያስ አፈወርቂን በክሬምሊን ቤተ መንግሥት ተቀብለው አነጋገሩ፡፡

የኤርትራ የማስታወቂያ ሚንስትር የማነ ገብረ መስቀል በትዊተር ገጻቸው ባወጡት ቃል ፕሬዚደንት ኢሳይያስ እና ፕሬዚደንት ፑቲን ዛሬ ረቡዕ ከቀትር በኋላ ባደረጉት ቆይታ የአገሮቻቸውን የሁለትዮሽ ግንኙነት፡ ዐለም አቀፍ ጉዳዮች እንዲሁም በጋራ ትኩረት በሚሰጧቸው ሁኔታዎች ዙሪያ በስፋት መወያየታቸውን አስታውቀዋል፡፡

አያያዘውም “የኤርትራ ፕሬዚደንት ኢሳይያስ በሩሲያ ፌዴሬሽን ያደረጉት የመጀመሪያ ጉብኝት ለሁለቱ ሀገሮች ግንኙነት ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ፕሬዚደንት ፑቲን አስምረውበታል” ብለዋል፡፡

“የሁለቱ ሀገሮች ግንኙነት ርምጃ ሙሉ በሙሉ አመርቂ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ” ፑቲን መናገራቸው አክለው “በመጪው ሐምሌ ወር ሞስኮ በምታስተናግደው ሁለተኛው የሩሲያ እና የአፍሪካ የመሪዎች ጉባዔ ላይ እንዲገኙ ጋብዘዋቸዋል” ብለዋል፡፡

የኤርትራ ፕሬዚደንት በበኩላቸው ጉብኝታቸው የሁለቱን ሀገሮች ከፍተኛ የአጋርነት እና የምክክር ግንኙነት የሚያንጸባርቅ መሆኑን መናገራቸውን የማስታወቂያ ሚኒስትሩ የማነ ገብረ መስቀል አመልክተዋል፡፡

XS
SM
MD
LG