በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፕሬዚደንት ትረምፕ ፖርቶ ሪኮን እየጎበኙ ነው


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ ዛሬ ማስከኞ ፖርቶ ሪኮን እየጎበኙ ናቸው።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ ዛሬ ማስከኞ ፖርቶ ሪኮን እየጎበኙ ናቸው። በከባድ አውሎ ንፋሳማ ዝናብ በተጎዱት ቴክሳስና ፍሎሪዳ ክፍላተ ሀገር የተካሄዱት ፈጥኖ ደራሽ ዕርዳታ ጥረቶች ያደነቁት ፕሬዚደንቱ ከሁለት ሳምንታት በፊት ሀሪኬይን ማሪያ በመታቻቸው ካሪቢያን አገሮች ዕርዳት ላይ የተሰማሩትን ቀዳሚ የዕርዳታ ሰራተኞች አመስግነዋል።

ፕሬዚደንቱ ከቀዳማዊት እመቤት መላኒያ ጋር ወደሳን ሁዋን ለመጓዝ ከዋይት ሃውስ ከመነሳታቸው አስቀድመው ዋይት ሃውስ ላይ ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃል

“ቴክሳስና ፍሎሪዳ ላይ ኤ ፕለስ … እጅግ በጣም ጥሩ ተብለናል። ልንገራችሁ ፖርቶ ሪኮ ላይም ከዚያ በከፋ ሁኔታ ውስጥ በዚያው ደረጃ የሠራን ይመስለኛል” ብለዋል።

ፕሬዚደንቱ በጉብኝታቸው ዋሽንግተን በሚገባ አልደረሰልንም ብለው ነቀፋ ያሰሙትን የሳን ሁዋን ከንቲባ ጨምሮ ከደሴቲቱ ባለሥጣናት ይነጋገራሉ፡፡

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG