በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኦባማ አዲስ አበባ ገቡ


የኢትዮጵያ አቀባበልና የኬንያ ጉብኝት ማጠቃለያ ዘገባ

ቦሌ ዓለምአቀፍ አይሮፕላን ጣቢያ - ሐምሌ 19/2007 ዓ.ም
ቦሌ ዓለምአቀፍ አይሮፕላን ጣቢያ - ሐምሌ 19/2007 ዓ.ም

please wait

No media source currently available

0:00 0:27:40 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ዛሬ፤ ሐምሌ 19/2007 ዓ.ም ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡

ሚስተር ኦባማ በአዲስ አበባ የሁለት ቀናት ቆይታቸው ወቅት ስለ ሽብርተኝነት፣ የሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ ጉዳይ እና የደቡብ ሱዳንን የርስ በርስ ጦርነት በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ይነጋገራሉ ተብሏል፡፡

ፕሬዚዳንት ኦባማ ቦሌ ዓለምአቀፍ አይሮፕላን ጣቢያ ሲደርሱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝና ከኢትዮጵያ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ተቀብለዋቸዋል፡፡

ከዚያም ከዲፕሎማሲ ተልዕኮ ባለሥልጣኖቻቸው ጋር ለመገናኘት ወደ አሜሪካ ኤምባሲ አምርተዋል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ዩናይትድ ስቴትስና ኬንያ በሽብር ፈጠራ ላይ በሚደረገው ዘመቻ በአንድ ላይ የቆሙ ናቸው ሲሉ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ አስታውቀዋል፡፡

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ትናንት ከኬንያ ባለሥልጣናት ጋር በተወያዩበት ጊዜ ሃገራቸው የምትሰጠውን ድጋፍ እንደሚያጠናክሩ ቃል ገብተዋል፡፡

ለሙሉው ዝርዝር የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

እስክንድር ፍሬው - ቦሌ ዓለምአቀፍ አይሮፕላን ጣቢያ - ሐምሌ 19/2007 ዓ.ም
እስክንድር ፍሬው - ቦሌ ዓለምአቀፍ አይሮፕላን ጣቢያ - ሐምሌ 19/2007 ዓ.ም

XS
SM
MD
LG