በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኦባማና የኃይለማርያም ጋዜጣዊ መግለጫ


የፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማና የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ ጋዜጣዊ መግለጫ
የፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማና የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ ጋዜጣዊ መግለጫ

በኢትዮጵያ ቀጣይ ዕድገት ሊኖር የሚችለው በመረጃዎች ፍሰትና በግልፅ የሃሣብ ልውውጥ ላይ ሲመሠረት መሆኑን ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ አሳስበዋል፡፡

please wait

No media source currently available

0:00 0:09:20 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

በኢትዮጵያ ቀጣይ ዕድገት ሊኖር የሚችለው በመረጃዎች ፍሰትና በግልፅ የሃሣብ ልውውጥ ላይ ሲመሠረት መሆኑን ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ አሳስበዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ይህንን የተናገሩት ዛሬ አዲስ አበባ ላይ ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ ጋር ሆነው ጋዜጣዊ መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነው፡፡

“የኢትዮጵያ ዕድገት መቀጠል የሚወሰነው በመረጃ በነፃነት መንሸራሸርና ሃሣቦችን በግልፅ መለዋወጥ በማስቻሏ ነው፡፡ ሁሉም ድምፆች ሲሰሙ፤ ሕዝቡ የፖለቲካ ሂደቱ አካል መሆኑን ሲያውቅ ሃገር ይበልጥ ጠንካራ፣ ይበልጥ ስኬታማ፣ ይበልጥ በፈጠራ ችሎታ የተሞላች ትሆናለች ብዬ አምናለሁ፡፡ በመሆኑም ኢትዮጵያ መልካም አስተዳደርን ለማሥረፅ፣ ሰብዓዊ መብቶችን፣ መሠረታዊ ነፃነቶችን ለማክበርና ዴሞክራሲን ለማጠናከር ልትወስዳቸው በሚገባ እርምጃዎች ላይ ተወያይተናል፡፡ ይህ ደግሞ ንግግሮቻችን ጥልቀት እያገኙ እንዲሄዱ የምንፈልግበት መስክ ነው፡፡ ምክንያቱም በኢትዮጵያ ተስፋና በሕዝቧ በብርቱ እናምናለን፡፡” ብለዋል ፕሬዚዳንት ኦባማ፡፡

ፕሬዚዳንቱ አክለውም አንዳንድ በኢትዮጵያ ሲንቀሳቀሱ የቆዩ ቡድኖችን አሸባሪዎች ለማለት መረጃ እንደሌለ የተናገገሩት ፕሬዚዳንት ኦባማ “ኢትዮጵያ ውስጥ በንቃት የሚንቀሣቀሱ በኢትዮጵያ መንግሥት አመለካከት ብርቱ ሥጋት የሚደቅኑ አንዳንድ ቡድኖች መኖራቸውን አውቃለሁ፡፡ የእኛ የሥለላ መረጃ ግን የሚጠቁመው ግን ቡድኖቹ የኢትዮጵያን መንግሥት ይቃወሙ እንጂ በሽብር ፈጠራ አድራጎት ውስጥ አለመግባታቸውን ነው፡፡ እኛ ይህንን የምንመዝንባቸው በጣም ግልፅ የሆኑ ደረጃዎችና መለኪያዎች አሉን፡፡ ሆኖም ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደጠቆምኩት በምክክሮቻችንና እየጠበቀ በሚሄደው የስለላ ትብብራችን ትክክለኛ ችግሮችና እውነተኛ የሽብር አድራጎቶች ባሉባቸው ማስረጃዎች እንዳሉ እናያለን፡፡” ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ ዴሞክራሲን ለመገንባት ነባሩ ኢዴሞክራሲያዊ ባህል ትልቅ ፈተና ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ ገልፀዋል፡፡

“በኢትዮጵያ ላይ የሚጠበቅባትና ዕውነታው ብዙ ጊዜ የተለያዩ መሆናቸውን ሙሉ በሙሉ እንረዳለን፡፡ ስለዚህ በችግሩ ላይ ለመሥራት እንፈልጋለን፡፡ ሥጋታችን ወይም ጉዳያችንም ነው፡፡ ይሁን እንጂ ይህ እያቆጠቆጠ ያለ ዴሞክራሲ መሆኑን ሰዎች እንዲገነዘቡልን እንፈልጋለን፡፡ በዚህች ሃገር ውስጥ በመቶዎች ዓመታት ከተቆጠሩ ዴሞክራሲያዊ ያልሆኑ ልማዶች እና ባሕል ነው እየወጣን ያለነው፡፡ በጥቂት አሥሮች ዓመታት ውስጥ፤ (በእኛ አጋጣሚ በሃያ የዴሞክራሲ ግንባታ ዓመታት፣) እኛ እየተጋፈጥናቸው ካለን አመለካከቶችና ችግሮች መላቀቅ ቀላል አይደለም፡፡” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ፡፡

ፕሬዚዳንት ኦባማና ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የሶማሊያና የደቡብ ሱዳንን ጉዳዮችም አንስተው ተነጋግረዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG