ኢትዮጵያ ከተጋረጠባት የሰላም እጦት እንድትወጣ የሃይማኖት አባቶች የፀሎት እና የሰላም ጥሪ አቅርበዋል።
የሃይማኖት አባቶቹ፣ ዛሬ በአዲስ አበባ በተካሔደ ዝግጅት ላይ ለተፋላሚ ሃይሎች የሰላም ጥሪ ያቀረቡ ሲኾን፣ የፀሎት አዋጅም አውጀዋል፡፡
በኢትዮጵያ የሲቪል እና የሙያ ማኅበራት ኮንግረስ አዘጋጅነት ሐሙስ ጥር 29 ቀን በአድዋ ድል መታሰቢያ አዳራሽ በተካሔደ አገራዊ የፀሎት እና የሰላም ጥሪ ዝግጅት ላይ የተገኙ የልዩ ልዩ ቤተ እምነቶች አባቶች ፀሎት ካደረጉ በኋላ ለምዕመናን እና ለተፋላሚ ወገኖች መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
መድረክ / ፎረም