ዋሺንግተን ዲሲ —
የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ዛሬ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል። ፕሬዚዳንት ኢሳያስና አብረዋቸው የሄዱት ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣኖች በኢትዮጵያ በአካሄዱት አጭር ጉብኝት ኦሞ በተደረገው የኩራስ ሱካር ፋብሪካ ምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ ተገኝተው፣ አርባ ምንጭን ጎብኝተዋል።
አዲስ አበባ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ጋር ሰፊ ንግግር አካሂደዋል ሲሉ የኤርትራ የማስታወቅያ ሚኒስትር አቶ የማነ ገብረ-መስቀል በትዊተር ገልፀዋል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ