በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሃማስ አሥራ አራት አሜሪካዊያንንም ገድሏል - ባይደን


ፕሬዚዳንት ባይደን እና ምክትል ፕሬዚዳንት ካማላ ሃሪስ
ፕሬዚዳንት ባይደን እና ምክትል ፕሬዚዳንት ካማላ ሃሪስ

ሃማስ ሰሞኑን በእሥራዔል ላይ በከፈተው ጥቃት ከተገደሉት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሲቪሎች መካከል አሥራ አራቱ አሜሪካዊያን መሆናቸውን የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አስታወቁ።

ፕሬዚዳንቱ ዛሬ (ማክሰኞ) ከቀትር በኋላ ከዋይት ሃውስ ቤተመንግሥት ባደረጉት ንግግር ሃማስ ፈፅሟል ባሉት “መልከብዙና ጫፈብዙ አስደንጋጭ ጥቃት” ምክንያት “ፍፁም ጋኔን” ሲሉ ጠርተውታል።

ፕሬዚዳንቱ ለእሥራዔል ያላቸውን ፅኑዕ ድጋፍ በገለፁበት ንግግራቸው “እሥራዔል ስናደርግ እንደቆየነው ሁሉ ዛሬም ወደፊትም እራሷን ትከላከላለች” ብለዋል።

እሥራዔል ጋዛ ሰርጥ ውስጥ ባካሄደችው የበቀል ድብደባ በመቶዎች የሚቆጠሩ ፍልስጥዔማዊያን መገደላቸውን አሶሲየትድ ፕሬስ አክሎ ዘግቧል።

የእሥራዔል የአየር ድብደባ እንደቀጠለ ሲሆን የሞቱ ቁጥር ሊያሻቅብ እንደሚችል የዜና ወኪሉ ጠቁሞ ብዙዎች ፍልስጥዔማዊያን ወደ መንግሥታቱ ድርጅት መጠለያዎች እየሸሹ መሆናቸውን አመልክቷል።

ፕሬዚዳንት ባይደን እና ምክትል ፕሬዚዳንት ካማላ ሃሪስ ዛሬ ረፋድ ላይ ለእሥራዔል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ደውለው አሁን ባለው ሁኔታ ላይ መምከራቸው ተዘግቧል።

እሥራዔልን ለመደገፍ መንግሥታቸውና ሌሎችም አጋሮች እየወሰዱ ስላሉት እርምጃ ባይደን የገለፁ ሲሆን ሃማስ በሲቪሎች ላይ አድርሷል የሚባሉ የማሰቃየት አድራጎቶች ልቦናን የሚያቆስሉ እንደሆኑ ተናግረዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG