ዋሽንግተን ዲሲ —
የዓለም ባንክ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በዓለም ደረጃ ሲሠራበት የቆየውን የድህነት መለኪያ ሠንጠረዥ፥ ከ 1 ዶላር ከ 25 ሳንቲም ወደ 1 ዶላር ከ 90 ከፍ አድርጓል። ድንገት ሲታይ በሰዎች የዕለት ገቢ ላይ የተደረገ ጭማሪ ቢመስልም፥ በእውን ግን ካለው ግሽበትና ሌሎች ሁኔታዎች ጋር ሲነፃጸር፥ ከቀድሞው ያነሰ ነው ይላሉ የኢኮኖሚ ባለሞያው ጃክሰን ሂክል (Jason Hickel)።