በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኮሮናቫይረስ ክትባት ሙከራ በዩናይትድ ስቴትስ


ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ፣ የኮቪድ-19 ክትባት መድሃኒት ይሆናሉ የሚል ተስፋ የተጣልባቸው ሁለት መድሃኒቶች፣ አስተማማኝነታቸውን ለማይት፣ ትናንት ሙከራ ተጀምሯል።

ሞደርና የተባለው የባዮቴክኖሎጂ ኩባንያ፣ አንድ አዲስ የኮሮናቫይረስ ክትባት መድሃኒት፣ በ30,000 ሙሉ ጤና ያላችው ጎልማሶች ላይ ሙከራ መጀመሩን አስታውቋል።

ከብሄራዊ የአለርጂና የተላላፊ በሽታዎች ተቋም ጋር በመተባበር፣ ሙከራው ትናንት የተጀመረው፣ በሳቫና ጆርጂያ መሆኑን ኩባንያው አስታውቋል። ሳቫና በሀገሪቱ ዙሪያ ካሉት፣ በርካታ የሙከራ ቦታዎች፣ አንዱ ነው ተብሏል።

ቀደም ሲል በተደረገው ሙከራ መሰረት፣ ከተሞከረባችው ስዎች መካከል፣ ከባድ የጎንዪሽ አንደምታ የገጠማቸው ስዎች እንደሌሉ ተገልጿል። የክትባቱ ሙከራ ከተደረገባቸው ሰዎች መካከል ከግማሽ በላይ ክትባቱን በተወጉበት ቦታ ላይ፣ ቀለል ያል ድካም፣ ራስ ምታት፣ የብርድ-ብርድና የሰውነት መቀጥቀጥ ስሜት እንደተሰማቸው ገልፀዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ የብሄራዊ የአለርጂና የተላላፊ በሽታዎች ተቋም ዳይሬክተር ዶ/ር አንተኒ ፋውቺ ትናንት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ የመጀመሪያው የክትባቱ ውጤት፣ እስከ መጪው ህዳር ወር ባለው ጊዜ ውስጥ ሊታወቅእንዳሚችል ጠቁመዋል።

ሙከራው ውጤታማ ከሆነ፣ ሞደርና በየአመቱ 500 ሚልዮን የክትባት መድሀኒት ሊያመርት ይችላል። በቀጣዩ አመት ደግሞ በየአመቱ፣ አንድ ቢልዮን ክትባት ሊያደርሰው እንደሚችል ፋውቺ ጠቁመዋል።

‘Pfizer’ የተባለ የዩናይትድ ስቴትስ ኩባንያ፣ ከጀርመኑ ‘BioNTech SE’ ጋር በመተባበር የሰሩት፣ የክትባት መድሃኒት ደግሞ፣ በዩናይትድ ስቴትስ ዙሪያ፣ በብራዚል፣ አርጀንቲናና ጀርመን፣ በ30,000 ሰዎች ላይ ሙከራ ያደርጋሉ።

በዓለም ዙሪያ፣ ወደ 150 የሚጠጉ የኮቪድ-19 የክትባት መድሃኒት ሙከራዎች፣ እየተካሄዱ መሆናቸው ታውቋል።

XS
SM
MD
LG