ዋሺንግተን ዲ.ሲ. —
ከአዲስ አበባ ከተማ ወጣ ብላ በምትገኘው የቡራዩ አካባቢ መገደሏ የተገለፀው የዕፅዋት ሥነ-ሕይወት አጥኝ ሻሮን ግሬይ የድህረ-ዶክትሬት ጥናት ላይ እንደነበረች ዩሲ ዴቪስ ተብሎ የሚታወቀው የካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ አስታውቋል።
የዶ/ር ሻሮን ግሬይ መገደል ዩኒቨርሲቲውን በእጅጉ እንዳሳዘነው ቃል አቀባዩ ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡
ግሬይ የተገደለችው ቡራዩ አካባቢ እየተጓዘች ሣለች ተሣፍራበት የነበረ መኪና ላይ በተወረወረ ድንጋይ መሆኑ ተዘግቧል፡፡
አብሯት የነበረ የዩኒቨርሲቲው ባልደረባ ጉዳት ሳይደርስበት ወደ ቤቱ ተመልሷል፡፡
የዩሲ ዴቪስ ቃል አቀባይ ለቪኦኤ በሰጡት መግለጫ ላይ የተጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡