በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የምትክል ፕሬዚዳንቷ ጉዞና የሃቫና ሲንድረም


ምክትል ፕሬዚዳንት ከማላ ኻሪስ

የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት ደቡብ ኤዥያን በመጎብኘት ላይ የሚገኙት ምክትል ፕሬዚዳንት ከማላ ኻሪስን የቬትናም ጉብኘት እንዲዘገይ ምክንያት የሆኑትንና የሃቫና ሲንድሮም በሚል የሚታወቁትን ሁለት የጤና ሁከቶችን መንስኤ መመርመር መቀጠላቸውን አስታውቀዋል፡፡

ምርመራው ገና በጅማሬ ላይ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ምክትል ፕሬዚዳንትዋ ከሲንጋፑር ወደ ቬትናም በሚያደርጉት ጉዞ የሚያፈጥረው ችግር ባለመኖሩ፣ ትላንት ማክሰኞ ወደዚያው እንዲያመሩ መደረጉም ተገልጿል፡፡

ከማላ ኻሪስ፣ ወደቡብ ኤዥያ የሚያደርጉት ጉዞ፣ ከአፍጋኒስታን ስደተኞችን በማውጣት ሂደት መካከል የሚደረግ ቢሆንም፣ የአሜሪካ የውጭ ፖሊሲ፣ አሁንም ለአጋሮች አለኝታ መሆኑን ለማስመገንዘብ መሆኑም ተዘግቧል፡፡

የሃቫና ሲንደሮም በመባል የሚታወቀው የጤና ሁከት፣ ቀደም ሲል በአሜሪካ ዲፕሎማቶችና በሌሎች የመንግሥት ሠራተኞች በኩባ ዋና ከተማ ሃቫና ውስጥ፣ በ2016 የተከሰተ አንጎልን የሚረብሽ የጤና ችግር መሆኑም ታውቋል፡፡

አስተያየቶችን ይዩ

XS
SM
MD
LG