በሳምባቸው የተፈጠረ ኢንፌክሽን በኩላሊታቸው ላይ ጉዳት ማድረሱን ተከትሎ ላለፉት ዐሥር ቀናት በሆስፒታል ሕክምና ሲደረግላቸው የቆዩት የሮማ ካቶሊክ ሊቀ ጳጳስ አባ ፍራንሲስ በተሻለ የጤና ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ቫቲካን አስታውቃለች።
"ሌሊቱን በጥሩ ሁኔታ አሳልፈዋል። አባ ፍራንሲስ እንቅልፍ መተኛት እና ማረፍ ችለዋል" ስትል ያስታወቀችው ቫቲካን፣ የ88 ዓመቱ ሊቀ ጳጳስ አሁንም አስጊ ሁኔታ ውስጥ ቢሆኑም አሁን እራሳቸውን ችለው እየተመገቡ መኾኑን እና ምን ዐይነት ሰው ሠራሽ ወይም ፈሳሽ ምግብ እየወሰዱ እንዳልኾነ ተገልጿል። በመልካም ኹኔታ ላይ ይገኛሉም ብሏል።
በሁለቱም ሳምባቸው ላይ ኒሞኒያ የተሰኘ የሳምባ ኢንፌክሽን ያጋጠማቸው አባ ፍራንሲስ ከፍተኛ መጠን ያለው ኦክሲጅን ሲሰጣቸው የቆዩ ሲሆን እሑድ እለት ከህመማቸው አገግመው በቅዳሴ ሥነ ስርዐት ላይ በንቃት መሳተፋቸው ተመልክቷል።
በቫቲካን ሁለተኛ ስፍራ ያላቸው ብፁዕ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን ትላንት እሑድ ምሽት በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የተካሄደውን የጸሎት ሥነ ስርዐት መምራታቸውም ተገልጿል።
መድረክ / ፎረም