በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አባ ፍራንሲስ ለብሮንካይትስ ሕክምና ሆስፒታል ገቡ 


ፎቶ ፋይል፦ የሮማ ካቶሊክ ሊቀ ጳጳስ አባ ፍራንሲስ
ፎቶ ፋይል፦ የሮማ ካቶሊክ ሊቀ ጳጳስ አባ ፍራንሲስ

የሮማ ካቶሊክ ሊቀ ጳጳስ አባ ፍራንሲስ፣ ብሮንካይተስ ለተሰኘ የመተንፈሻ አካል ኢንፌክሽን ሕክምና ዛሬ አርብ ጠዋት ሆስፒታል መግባታቸውን ቫቲካን በአወጣው መግለጫ አስታውቋል።

"አባ ፍራንሲስ ዛሬ ጠዋት የተለመደውን የቤተክርስቲያን ሥርዓታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ አስፈላጊ ለሆኑ ምርመራዎች እና የብሮንካይትስ ሕክምና ሆስፒታል ገብተዋል" ሲል በመግለጫው የገለጸው ቫቲካን፣ አሁንም በሆስፒታል እንደሚገኙ አመልክቷል።

በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ አባ ፍራንሲስ ለምዕመናኑ ጠንካራ የጉንፋን በሽታ እንደያዛቸው ተናግረው የነበረ ቢሆንም፣ ቫቲካን ሕመማቸው በቫይረስ ወይም በባክቴርያ አማካኝነት የሚከሰት የሳምባ በሽታ ወይም ብሮንካይትስ መሆኑን አስታውቋል።

አባ ፍራንሲስ ዛሬ ጠዋት ሆስፒታል እስከሚከቡ ድረስ፣ ቫቲካን በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ሆነው የዕለት ተዕለት ሥራቸውን ሲያከናውኑ የቆዩ ሲሆን ዛሬ ጠዋት ከስሎቫኪያን ጠቅላይ ሚኒስትር ሮበርት ፊኮው ጋራ ተገናኝተዋል።

የ88 ዕድሜ ያላቸው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ ፍራንሲስ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ በኢንፍሉዌንዛ እና ተያያዥ የጤና ችግሮች ሲሰቃዩ መቆየታቸው ይታወሳል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG