በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“ሁላችንም ልባችን ቤተልሄም ነው” አቡነ ፍራንሲስ


የሮማው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት አቡነ ፍራንሲስ
የሮማው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት አቡነ ፍራንሲስ

የሮማው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት አቡነ ፍራንሲስ በፈረንጆች ገና ዋዜማ ስብከታቸው

“አሁንም የቀጠሉት የትጥቅ ግጭቶች ኢየሱስ ክርስቶስን በዓለም ላይ ስፍራ እያሳጡት ነው” ሲሉ ተናገሩ፡፡

አቡነ ፍራንሲስ ኢየሱስ ክርስቶስ በቤተልሔም መወለዱን አስታውሰው "ልባችን፣ በከንቱ የጦርነት አመለካከት ምክንያት የሰላሙ ንጉሥ አሁንም ከሚገፋበት፣ ከቤተልሔም ጋር ነው" ሲሉም እ.አ.አ ጥቅምት 7 ሐማስ በእስራኤል ባደረሰው ጥቃት ምክንያት የተጀመረውን ጦርነት አስታውሰዋል።

አቡነ ፍራንሲስ ትናንት ዕሁድ የገና ዋዜማ የቅዳሴ ስነ ስርዓት የመሩት ወደ 6 ሺህ 500 ምዕመናን በተገኙበት በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ላይ ሲሆን፣ ስነ ስርዓቱ ሲጀመር የክርስቶስን ምስል የያዘው ሐውልት በአረንጓዴ እና ነጭ አበባዎች ተሸልሞ ታይቷል። የተለያዩ የዓለም ክፍሎችን የሚወክሉ ህፃናትም አበባዎችን በወርቅ ዙፋኑ ዙሪያ አስቀምጠዋል።

በጦርነት ከሚሰቃዩ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ጋር በቅርበት አብረናቸው ነን። ፍልስጤምን፣ እስራኤልን፣ ዩክሬንን እናስባለን። በመከራ፣ በረሃብ፣ በባርነት የሚሰቃዩትንም እናስባለን"

ኢየሱስ ክርስቶስ፣ የንጉሥ ዳዊትን ኃይል ለማጠናከር ታስቦ በተካሄደ የህዝብ ቆጠራ ወቅት መወለዱን ያስታወሱት የሮማው ሊቃነ ጳጳሳት፣ "ዓለም፣ ስኬት በውጤት እና በቁጥር በሚለካበትን ዓለማዊ ኃይል፣ ዝና እና ክብር ፍለጋ ተጠምዷል" ብለው “በንፅፅር፣ ኢየሱስ ስጋ ለብሶ ወደ ዓለም የመጣው ትህትና ተላብሶ ነው” በማለት አስታውሰዋል።

"በጦርነት ከሚሰቃዩ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ጋር በቅርበት አብረናቸው ነን። ፍልስጤምን፣ እስራኤልን፣ ዩክሬንን እናስባለን። በመከራ፣ በረሃብ፣ በባርነት የሚሰቃዩትንም እናስባለን" ያሉት አቡነ ፍራንሲስ "የሰውን ልብ ለራሱ የወሰደ አምላክ፣ ለሰው ልጅም ሰብዓዊነትን እንዲያለብስ ይሁን" ሲሉ ፀልየዋል።

በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡት በሺዎች የሚቆጠሩ ምዕመናን ተገኝተው ባደመጡት ስብከታቸው ምዕመናኑ የገናን በዓል፣ ቅጥ ካጣ ቁሳዊ የገበያ ልማድ ጋር እንዳያምታቱት እና የበዓሉ ሀይማኖታዊ ምክንያት እንዲያስቡት ጠይቀዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG