በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሮማው ካቶሊክ ሊቀ ጳጳስ የእስረኞችን እግር አጠቡ


 የሮማው ካቶሊክ አቡን ፍራንሲስ በሮም፣ ጣሊያን፤ እአአ መጋቢት 29/2024
የሮማው ካቶሊክ አቡን ፍራንሲስ በሮም፣ ጣሊያን፤ እአአ መጋቢት 29/2024

በመጪው እሁድ የሚከበረው የፈረንጆቹ ፋሲካ ሃይማኖታዊ ሥነ ስርዓት አካል በሆነው ፀሎተ ሐሙስ፣ የሮማው ካቶሊክ አቡን ፍራንሲስ በሮም በሚገኝ እስር ቤት ያሉ 12 ሴቶችን እግር አጥበው ስመዋል።

እየሱስ ክርስቶስ ከመሰቀሉ በፊት በነበረው የመጨረሻው ምሽት የደቀ መዛሙርቱን እግር ማጠቡን ለማስታወስ በክርስትና እንምነት ተከታዮች ዘንድ የሚከናወነውን ሥነ ስርዓት ለመፈፀም፣ የሮማው አቡን በሮም ዳርቻ በሚገኝ የሴቶች እስር ቤት ተገኝተዋል።

ሰሞኑን ብሮንካይተስ እና ጉንፋን ያሰቸገራቸው አቡኑ፣ በሕዝባዊ ክንውኖች ላይ ሳይሳተፉ ቀርተው ነበር። ደከም ስላሉም በተንቀሳቃሽ ወንበር ላይ በመሆን ነው የእስረኞቹ እግር ያጠቡት፡፡

በጣሊያን ካሉ ትላልቅ እስር ቤቶች አንዱ በሆነውና በሮም ዳርቻ ባለው ረቢባይ እስር ቤት በተለያዩ ወንጀሎች ጥፋተኛ የተባሉ 370 ሴት እስረኞች ይገኛሉ።

የእግር አጠባውን ሥነ ስርዓት ከቤ/ክ ውጪ ሲያከናውኑ አቡነ ፍራንሲስ የመጀመሪያው ናቸው። ይህም የቦነስ አይረስ ሊቀ ጳጳስ በነበሩበት ግዜ የጀመሩት እንደሆነ ታውቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG