የሮማው ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ አቡነ ፍራንሲስ፣ ዛሬ ሀሙስ፣ በኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ዋና ከተማ ኪንሻሳ በሚገኘው ስቴድዮም ውስጥ፣ ለተሰበሰቡ በ10ሺዎች ለሚቆጠሩ ወጣቶች፣ የሰላምና እርቅ መልዕክት አሰምተዋል፡፡
የሊቀ ጳጳሱ የኮንጎ ጉብኝት በኪንሻሳ ሦስተኛ ቀኑን ያስቆጠረ ሲሆን በትናንቱ ውሏቸውም በዋና ከተማዪቱ በሚሊዮን ከሚቆጠሩ አማኞች ጋር የጸሎት ሥነ ስርዓት ማካሄዳቸው ተነግሯል፡፡
ሊቀ ጳጳሱ ነገ አርብ ለተከታዩ ጉብኝታቸው ወደ ደቡብ ሱዳን እንደሚያቀኑም ተመልክቷል፡፡