በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አባ ፍራንሲስ የኢየሱስ ክርስቶስን የልደት በዓል ምክንያት በማድረግ ለዓለም ሰላም ፀለዩ


የሮማው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት አባ ፍራንሲስ
የሮማው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት አባ ፍራንሲስ

የሮማው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት አባ ፍራንሲስ፣ በኢየሩሳሌእም ሰላም፣ በኮሪያው ባሐረ ገብ መሬትም መረጋጋት ይሆን ዘንድ ጥሪ አሰሙ።

የሮማው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት አባ ፍራንሲስ፣ በኢየሩሳሌእም ሰላም፣ በኮሪያው ባሐረ ገብ መሬትም መረጋጋት ይሆን ዘንድ ጥሪ አሰሙ።

አቡኑ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ዛሬ እየተከበረ ያለውን የኢየሱስ ክርስቶስን የልደት በዓል ምክንያት በማድረግ ነው፣ ለኢየሩሳሌምና ለመላው ዓለም በሚል ቃለ ምዕዳንና ጥሪያቸውን ያቀረቡት።

አባ ፍራንሲስ በእንዲህ ዓይነቱ ታላቅ በዓል መልዕክታቸውን ከሚያስተላልፉት ከተለመደው ከቅዱስ ጴጥሮስ ቤተ ክርስቲያን ዓውደ ምሕረት ባሰሙት ቃል፣ በእስሥራኤልና በፍልስጥኤማውያን መካከል የሰፈነው ውጥረት በሰላማዊ ድርድር እንዲረግብና፣ ሁለቱ ሕዝቦች በመቻቻል የሚኖሩበት ሁኔታ እንደሚፈጠር ተስፋቸውን ገልፀዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ ኢየሩሳሌምን በእሥራኤል ዋና ከተማነት በማወቋ፣ ውሳኔው ፍልስጥኤማውያንን እንዳስቆጣ አይዘነጋም።

ዛሬ በመላው ዓለም የሚካሄደው አለመረጋጋት ለግጭቶች መንስዔ ሆኖ በዚህም አያሌ ህፃናት ሕይወታቸውን እንደሚያጡ ያመለከቱት አባ ፍራንሲስ፣ ከዚህ አኳያ በተለይም በኮሪያው ባሕረ ገብ መሬት ያለውን የጦርነት ሥጋት በምሳሌነት ጠቅሰዋል።

ይህ የጦርነት ሥጋት ለማንኛውም ወገን የማይበጅ በመሆኑ፣ ሰላምና መረጋጋት ይሰፍን ዘንድ ተግተን ልንጸልይ ይገባል ሲሉም፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት አባ ፍራንሴስ አበክረው አሳስበዋል።

አባ ፍራንሲስ የኢየሱስ ክርስቶስን የልደት በዓል ምክንያት በማድረግ ለዓለም ሰላም ፀለዩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:02 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG