በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የቀድሞ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክት ቀብር ተፈጸመ


የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የቀድሞ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክት ቀብር ተፈጸመ
የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የቀድሞ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክት ቀብር ተፈጸመ

ቀደም ብሎ ብዙ ሺህ ሀዘንተኞች በቫቲካን ቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በፖፕ ቤኔዲክት የፍትሀት እና ሽኝት ሥነ ስርዓት ላይ ተገኝተዋል፡፡

በቤተ ክርስቲያኒቱ ታሪክ በራሳቸው ፈቃድ በጡረታ በመገለል ታሪክ ለሰሩት ሰው ሽኝት የተከናወነውን የቅዳሴ ሥርዓት የመሩት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ናቸው፡፡

ዜና ዕረፍታቸው በተሰማበት ጊዜ በሽኝታቸው ላይ 60 ሺህ ሰው ይገኛል ተብሎ ተገምቶ የነበረ ቢሆንም ዛሬ ግን ፖሊሶች 100 ሺህ ሰው ይገኛል ብለው እንደሚጠብቁ ነበር የተናገሩት፡፡

ሟቹ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የቀብር ሥነ ስርዓታቸው ቀለል ያለ እንዲሆን ጠይቀው የነበረ ሲሆን የቫቲካን ባለሥልጣናትም በመጠነኛ ሥነ ስርዓት ለማከናወን ጥረት አድርገው ነበር፡፡

ሆኖም ከዓለም ዙሪያ ርዕሳነ ብሄራት፡ የንጉሣዊ ቤተሰብ አባላት፡ በብዙ ሺህ የተቆጠሩ የቤተ ክርስቲያኗ ምእመናን ተገኝተዋል፡፡

ከትውልድ ሀገራቸው ከባቫሪያ ብዙዎች የባህል ልብሶቻቸውን ለብሰው ለሽኝቱ ተገኝተዋል፡፡

የቀድሞው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በተወለዱ በዘጠና አምስት ዓመታቸው ያረፉት ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ የፈረንጆች ገና ዋዜማ ዕለት ነው፡፡

XS
SM
MD
LG