በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሮማው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት አባ ፍራንሲስ የቺሌ ጉብኝት

የሮማው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት አባ ፍራንሲስ
የሮማው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት አባ ፍራንሲስ

የሮማው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት አባ ፍራንሲስ በመጀመሪያው የቺሌ ጉብኝታቸው፣ ሕፃናት ላይ በካህናት ለደረሰው ወሲባዊ ወከባ ምሕረት ጠየቁ። ይህ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያንን ክብር ያጎደፈ የተባለው ቅሌት "የማይጠገን ጉዳት" እንደሆነና፤ በአቡኑ ጉብኝት ላይም መጥፎ ገፅታ እንዳሳደረ ተነግሯል።

የሮማው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት አባ ፍራንሲስ በመጀመሪያው የቺሌ ጉብኝታቸው፣ ሕፃናት ላይ በካህናት ለደረሰው ወሲባዊ ወከባ ምሕረት ጠየቁ። ይህ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያንን ክብር ያጎደፈ የተባለው ቅሌት "የማይጠገን ጉዳት" እንደሆነና፤ በአቡኑ ጉብኝት ላይም መጥፎ ገፅታ እንዳሳደረ ተነግሯል።

ይቅርታ መጠየቅና ጉዳተኞቹንም ለመደገፍ አስፈላጊ የሆነውን ጥረት ሁሉ ማድረግ ትክክለኛ እርምጃ እንደሆነ የተናገሩት አባ ፍራንሲስ፣ ይህ ዓይነቱ አድራጎት ዳግም እንደማይፈጸምም ገልፀዋል።

አቡኑ፣ ሳንቲያጎ ውስጥ የቺሌው ፕሬዚደንትና ሌሎችም ከፍተኛ ባለሥልጣናት በተገኙበት ባሰሙት ንግግራቸው ውስጥ፣ ከዚህ ቀደም በዚሁ የወሲብ ቅሌት ስማቸው የተነሳውንና በዕድሜ ልክ ንሥሐና ፀሎት ውስጥ እንዲሆኑ የተበየነባቸውን ቄስ፣ ፈርናንዶ ኻራዲማን በስም አልጠቀሱም።

የቄስ ካራዲማ ሰለባዎች፣ ተደጋጋሚ ዕሮሮና ክሥ ለቤተ ክርስትያን ባለሥልጣናት ሲያቀርቡ ኖረው፣ እአአ በ2010 በይፋ ማጋለጣቸው አይዘነጋም።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG