ዋሺንግተን ዲሲ —
ኢትዮጵያ እና ኤርትራ በመካከላቸው ሰላም ለመገንባት ሊነጋገሩ ፈቃደኛ መሆናቸው መልካም ዜና ነው ሲሉ የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት አቡነ ፍራንሲስ አድናቆታቸውን ገለጹ።
አቡነ ፍራንሲስ ትናንት ዕሁድ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን ብዙ ግጭቶች ባሉበት ባሁኑ ወቅት ታሪካዊ ሊባል የሚችል የሰላም ጥረት ስናይ ደግሞ የመናገር ኃላፊነት አለብን ብለዋል።
የኤርትራ መንግሥት ልዑካን በአዲስ አበባ ያደረጉትን ጉብኝት ተከትሎ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁ እንዳስታወቁት የሁለቱ ሀግሮች መሪዎች በቅርቡ ተገንኝተው ይነጋገራሉ። አቡነ ፍራንሲስ ሁለቱ መንግሥታት ከሃያ ኦመታት በኋላ አብረው ስለሰላም መናገራቸው ለአፍሪካ ቀንድ ሀገሮች እና ለአጠቃላዩ የአፍሪካ አህጉር የተስፋ ብርሃን እንደሚፈነጥቅ ተስፋ እንዳላቸው ገልጸዋል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ