በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሊቢያ እሥር ቤቶች


ፎቶ ፋይል፦ የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ
ፎቶ ፋይል፦ የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ

ሊቢያ ውስጥ በሚገኙ ማጎሪያ ቤቶች ያሉት በሺህዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች ያሉበት ሁኔታ ከገሃነመ እሳት የሚቆጠር ነው ሲሉ የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ አሳሰቡ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ይህን ያሳሰቡት የዛሬ ሰባት ዓመት በዛሬዋ ዕለት ስደተኞች ከሰሜን አፍሪካ በስቃይ ጉዞ አውሮፓ የሚደርሱባትን የጣሊያኑዋን ደሴት ላምፔዱሳን የጎበኙበትን ዕለት ምክንያት በማድረግ ነው።

በጉብኝታቸው ከስደተኞች ጋር የተነጋገሩ ሲሆን የእሥር ካምፖቹ እንዲዘጉ ተማጽኖ አሰምተዋል፤ ስለስደተኞች ስቃይ የሰፈነው ዓለምቀፍ ደንታ ቢስነት ይቁም ሲሉ መማጸናቸው ይታወሳል።

XS
SM
MD
LG