በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ማይክ ፓምፔዮ ሱዳን ገቡ


የትረምፕ አስተዳደር የአረብ አገራት ከእስራኤል ጋር ያላቸውን ግንኙነት መልካም ለማድረግ ግፊት እያደረጉ ባሉበት ወቅት የአሜሪካው የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ማይክ ፓምፔዮ በዛሬው እለት ሱዳን ገብተዋል።

ፓምፔዮ በሱዳን ቆይታቸው ከጠቅላይ ሚኒስቴር አብደላ ሃምዶክ እና የሉዓላዊ መማክርት ሊቀምበር ጄነራል አብደል ፈታህ አል ቡርሀን ጋር ይገናኛሉ።

ሱዳን ከእስራኤል ጋር ከሚኖራት ግንኙነት በተጨማሪ፣ ፓምፔዮ አሜሪካ ለሱዳንን የሽግግር መንግስት የምታደርገውን ድጋፍ በምትቀጥልበት ሁኔታ ላይም እንደሚወያዩ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሀምዶክ ወደ ስልጣን የመጡት፣ ከ30 አመት በላይ ስልጣን ላይ የቆዩት የቀድሞው ፕሬዝዳንት ኦማር አልበሽር በደረሰባቸው ተቃውሞ ከስልጣን ከወረዱ በኃላ ባለፈው አመት ነሐሴ ላይ ነው።

ፓምፔዮ ሰኞ እለት ጉብኝታቸውን ከእስራኤል በጀመሩበት ወቅት ከእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስቴር ቤንጃሚን ኔትናሁ ጋር ተገናኝተዋል። በወቅቱ ባደረጉት ንግግርም አሜሪካ ከተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ጋር ያላትን የመሳሪያ ልውውጥ ስምምነት በመጠቀም በመካከለኛው ምስራቅ የእስራኤል ወታደራዊ የበላይነት እንዲጠበቅ እንደምትጥር ተናግረዋል።

አሜሪካ ለእስራኤል ወታደራዊ ቴክኖሎጂና ስልታዊ ድጋፎችን የማድረግ የህግ አስገዳጅነት አለባት። ያንን ማክበራችንን እንቀጥላለንም ብለዋል።

ፓምፔዮ አክለው አሜሪካ ከተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ጋር በፀጥታ ጉዳዮች ላይ ከ 20 አመት በላይ አብራ መስራቷንና ወታደራዊ ድጋፍ እንደምታደርግ ገልፀዋል።

ፓምፔዮ በመጪው ቀናት ወደ ባህሬንና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እንደሚጓዙና የቀጠናው የፀጥታ ጉዳይና እስራኤል በአካባቢ ካሉ አረብ አገራት ጋር ያላት ግንኙነት የሚጠናከርበት ጉዳይ ዋና የመወያያ አጀንዳቸው እንደሚሆን ተገልጿል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ማይክ ፓምፔዮ ሱዳን ገቡ
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:54 0:00


XS
SM
MD
LG