በኢትዮጵያ ተባብሶ ለቀጠለው ግጭት እና አለመረጋጋት፣ ብሔርን ማዕከል ያደረጉ ትርክቶች ምክንያት ናቸው፤ ሲሉ፣ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ተናገሩ፡፡
ግጭቶቹን በዘላቂነት ለመፍታትም፣ ሐቀኛ ሰላማዊ ድርድር እና ምክክር ማካሔድ እንደሚያስፈልግ፣ አመራሮቹ አመልክተዋል፡፡
የሰላም ሚኒስቴር በበኩሉ፣ ለሕዝቦች አለመግባባት እና ግጭት መነሻ የኾኑ ትርክቶችን በማረቅ የጋራ ሀገራዊ ማንነትን በሚገነቡ አስተሳሰቦች ላይ እየሠራ እንደኾነ አስታውቋል፡፡
አስማማው አየነው፣ የኢዜማ እና የኢሶዴፓ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችን፣ እንዲሁም የሰላም ሚኒስቴር ዴኤታን አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ አዘጋጅቷል፡፡
መድረክ / ፎረም