ኒው ዮርክ ከተማ አካባቢ ፖሊዮ መታየቱን ተከትሎ ነዋሪዎች ክትባት እንዲወስዱ ባለሥልጣናቱ እየወተወቱ ነው።
የኒው ዮርክ ከተማ አቅራቢያ ዌስትዋተር የሚባል አካባቢ ሹማምንት ፖሊዮ መታየቱን ካሳወቁበት ካለፈው ወር ቀደም ብሎም ቫይረሱ ይገኝ እንደነበር የተናገሩት የጤና ባለሥልጣናት ቫይረሱ ሰኔ ውስጥ ከተወሰደ ናሙና ላይ መገኘቱ ማሳያ እንደሆነ አመልክተዋል።
የፖሊዮ ቫይረስ በዌስትዋተር ኒው ዮርክ መታየቱ ሌሎች ተጨማሪ ሰዎች ተውሳኩን በእዳሪ አማካይነት ሳያሠራጩ እንዳልቀሩ እንደሚጠቁም የአሜሪካ የበሽታዎች መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከላት (ሲዲሲ) አስታውቋል።