በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ናይሮቢ ፍርድ ቤት ውስጥ አንድ ፖሊስ ተኩሶ ዳኛዋን አቆሰለ


ማካራዳራ ፍርድ ቤት ናይሮቢ፤ ኬኒያ
ማካራዳራ ፍርድ ቤት ናይሮቢ፤ ኬኒያ

ትላንት ሐሙስ ኬኒያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ውስጥ አንድ ፖሊስ ፍርድ ቤት ውስጥ ጥይት ተኩሶ የችሎቱን ዳኛ አቆሰላቸው። ድርጊቱን የፈጸመውን ፖሊሳ ሌሎች ፖሊሶች ወዲያው በጥይት መትረው እንደገደሉትም ከፍርድ ቤቱ የተሰጠው መግለጫ አመልክቷል።

የማካራዳራ ፍርድ ቤት ዳኛ ሞኒካ ኪቩቲ ላይ ተኩሶ ያቆሰላቸው ፖሊስ እስር ላይ የሚገኙት ባለቤቱ በዋስ ለመለቀቅ ያቀረቡትን ማመልከቻ ዳኛዋ ውድቅ ካደረጉት በኋላ መሆኑን መግለጫው ጨምሮ አመልክቷል። በጊዜው በተደረገው የተኩስ ልውውጥ የቆሰሉት ዳኛ እና ሌሎች ሦስት ፖሊሶች በሆስፒታል በሕክምና እየተረዱ መሆናቸው እና በአሁኑም ሰአት በደህና ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል።

ሮይተርስ የዜና ወኪል ባገኘው የፖሊስ ሪፖርት መሠረት የፖሊሱ ባለቤት 2 ነጥብ 9 ሚሊዮን የኬኒያ ሺሊንግ (22 ሺህ ዶላር) አጭበርብረው መውሰዳቸውን አምነዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG