በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በፈረንሳይ ሁለት ሴቶች በስለት ወግቶ የገደለው ታስሮ ተለቀቀ

ፈረንሳይ ማርሴይ ከተማ ውስጥ ትናንት ዕሁድ ሁለት ሴቶች በስለት ወግቶ የገደለው አጥቂ ጥቃቱን ከመፈፀሙ ሁለት ቀን በፊት ፖሊሶች አስረው የለቀቁት መሆኑ ተገለጠ።

ፈረንሳይ ማርሴይ ከተማ ውስጥ ትናንት ዕሁድ ሁለት ሴቶች በስለት ወግቶ የገደለው አጥቂ ጥቃቱን ከመፈፀሙ ሁለት ቀን በፊት ፖሊሶች አስረው የለቀቁት መሆኑ ተገለጠ።

የፈረንሳይ ባለሥልጣናት እንደተናገሩት የተለያዩ ስሞች የሚጠቀመው ሰውዬ ዓርብ ዕለት የሊዮን ከተማ ፖሊሶች ከመደብር ዕቃ በመስረቅ ተጠርጥሮ ይዘውት በኋላ ግን በቂ ማስረጃ ባለመቅረቡ ለቀውታል።

በዘገባዎች መሰረት ሰውየው ማርሴይ ዋናው ባቡር ጣቢያ ላይ አላህ ዋ ክበር እያለ እየጮኸ ሴቶቹን በስለት ከወጋ በኋላ ፖሊሶች በጥይት መትተው ገድለውታል።

የእስልምና መንግሥት ብሎ ራሱን የሚጠራው ቡድን በራሱ የዜና አውታር በኩል ለማርሴዩ ጥቃት ኃላፊነት ወስዷል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG