በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ታዋቂው የፊልም ተዋናይ አሌክ ቦልድዊን ለፊልም ቀረጻ በተኮሰው መሳሪያ የሰው ህይወት አለፈ


ተዋናይ አሌክ ቦልድዊን
ተዋናይ አሌክ ቦልድዊን

ታዋቂው የፊልም ተዋናይ አሌክ ቦልድዊን ኒው ሜክሲኮ ውስጥ ፊልም ቀረፃ ላይ ሳለ አረር አልባ /በቴአትር ጭውውቶች ላይ መጠቀሚያ ወይም የሩጫ ማስጀመሪያ ዓይነት የሚያስፈነጠር አረር የሌለው/ መስሎት በስህተት በተኮሰው እውነተኛ ጥይት የጎረሰ ሽጉጥ የቀረፃው የፎቶግራፊ ዳይሬክተር ተገደለች። የፊልሙ ዳይሬክተር በዚሁ አጋጣሚ ምክንያት ቆስሏል።

አደጋው የተከሰተው አሌክ ቦልድዊን በዋና ተዋናይነት የሚጫወትበት "ረስት" የተባለ ፊልም ደቡብ ምዕራቧ ኒው ሜክሲኮ ውስጥ እየተቀረጸ በነበረበት ወቅት መሆኑን ፖሊሶች ትናንት አስታውቀዋል።

የሳንታ ፌ ከተማ ፖሊስ አዛዝ ባወጡት መግለጫ አሌክ ቦልድዊን ከያዘው መሳሪያ በተተኮሰ ጥይት ሄይሊና ኸቺንግስ እና ጆል ሱዛ እንደተመቱ ገልጸዋል።

የምስል ቀረጻ ዳይሬክተር የነበረችው የ42 ዓመቷ ሄይሊ ሆስፒታል ብትወሰድም ህይወቷን ማትረፍ እንዳልተቻለ እና የፊልሙ ዳይሬክተር የአርባ ስምንት ዓመቱ ሱዛ ህክምና ላይ መሆኑን እና በከባድ ሁኔታ ላይ እንዳለ ፖሊስ አስታውቋል።

አደጋው የደረሰው ሳንታ ፌ ከተማ አቅራቢያ በሚገኝ በሆሊውድ የፊልም አዘጋጆች የሚዘውተር "ቦናንዛ ክሪክ ራንች " የተባለ የቀረጻ ስፍራ ሲሆን ክስ አልተመሰረተም፤ ምርመራ እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል።

XS
SM
MD
LG