በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን አንድ ፖሊስ በተቃዋሚው መድረክ ደጋፊ መገደሉን ዘገበ


Negaso Gidada
Negaso Gidada

ውንጀላው የቀረበበት የመድረክ ፓርቲ ጉዳዮ በገለልተኛ ወገን እንዲጣራ ጠይቛል።

በኦሮሚያ ክልል በምእራብ ሸዋ ዞን ሶስት የኦሮሞ ህዝብ ኮንግረስ አባላት ኮንስታብል ሀሰን ረጋሳ የተባሉ የፖሊስ ባልደረባን መግደላቸውን የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ዘገበ።

በኢሉገላን ወረዳ ኢያጂ 01 ቀባሌ የደረሰው ወንጀል በአሰቃቂ ሁኔታ በጩቤ መፈጸሙን የመንግስቱ ልሳን የሆነው ኢ.ቲ.ቪ. አስታውቛል።

ሶስቱ ተጠርጣሪዎች የስምንት የተቃዋሚ ፓርቲዎች ጥምረት የሆነው የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ፓርቲ አካል ኦ.ህ.ኮ. አባላት መሆናቸውን ዘገባው ጨምሮ ገልጿል።

Negaso Gidada
Negaso Gidada

ተጠርጣሪዎቹ ብርሃኑ ሸንተማ፣ ታሪኩ ጌታቸውና ፍሮምሳ ቦጋለ መሆናቸውን የፖሊስ የምርመራ መዝገብ ያትታል።

“የአካባቢ ሰላም በሚጠብቁ የፖሊስ አባላት አሉ። እነዚህን መደብደብ ወይንም በመግደል አለበለዚያም መዝረፍ ያስፈልጋል” የሚል ተልእኮ እንዳላቸው የኢ.ቲ.ቪ ዘገባ አትቷል። ይህንንም ተጠርጣሪዎቹ ማመናቸውን ዘገባው ጠቁሟል።

ውንጀላው የቀረበበት የመድረክ ፓርቲ ወንጀሉን የፈጸሙት የየትኛውም ፓርቲ አባላት ይሁኑ ድርጊቱን እንደሚያወግዝ ገልጧል።

“እኛ ስለጉዳዩ የሰማንው ትናንትና በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን …ጉዳዩ ሲዘገብ መዋሉን ነው የምናውቀው” በማለት የመድረኩ ቃል አቀባይ ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ተናግረዋል።

ጉዳዮን በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ከሰማ ወዲህ መድረክ አባሉ ከሆነው ኦ.ህ.ኮ ጋር በመሆን በማጣራት ላይ መሆኑን ዶክተር ነጋሶ ገልጸዋል። መድረክ ድርጊቱን እስኪያጣራ ድረስ ስለተፈጠረው ነገር በእርግጠኝነት ለመናገር እንደሚቸገርም ተናግረዋል። “መድረክ ከአላማውና ከቆመለት የሰው ልጆች መብት ወይንም ህይወት ከማስጠበቅ አኳያ ፈጽሞ እንዲህ አይነት አስነዋሪ ወንጀል እንዲፈጸም የማይፈልግና በጽኑ የሚያወግዝ መሆኑን እንገልጻለን።”

መድረክ ጉዳዩ በገለልተኛ አካላት እንዲጣራ ጠይቛል።

ዝርዝሩን የአማርኛ ዘገባ ለማዳመጥ እዚህ ይጫኑ።

XS
SM
MD
LG