በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፖሊሶች በሲቪሉ ህዝብ ላይ የሚያደርሱት በደል - በኬንያ


ኬንያ ውስጥ ፖሊሶች በሲቪሉ ህዝብ ላይ የሚያደርሱት በደል እየከፋ መሄዱን የኬንያ ነፃ የፖሊስ ክፍል ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን ተናግሯል።

ኬንያ ውስጥ ፖሊሶች የሚያደርሱት በደል ካለፍርድ መግደልንና አስገድዶ ማሰወርን እንደሚያካትት የቁጥጥሩ ባለሥልጣን ጠቁሟል።

የቁጥጥሩ አካል ትላንት ያወጣው ዘገባ በኬንያ ፖሊስ ኃይል የተፈጸሙ ያለቸውን ከ3,000 በላይ የበደል ተግባሮችን ይፋ አድርጓል። በደሎቹ በአብዛኛው የሚፈጸሙት በደሳሳ ሰፈሮች አከባቢ ነው ይላል ዘገባው።

እአአ 2019 ታህሳስ ወር በአበቃው 3,200 የሚሆኑ ስዎች በፖሊሶች በደል ተፈጽሞብናል የሚል ክስ አቅርበዋል ይላል የፖሊሶች ተግባርን የሚከታተለው ነጻ አካል። ከስድስት ዓመታት በፊት ተመሳሳይ ክስ ካቀረቡት ሰዎች ብዛት በስድስት እጥፍ እደጨመረ ተገልጿል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG