በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኤርትራውያን በሄግ ተጋጩ


በተፈጠረው ግጭት በርካታ የፖሊስ መኪኖችና አንድ አውቶብስ በእሳት ጋይቷል፤ ሄግ፣ ኔዘርላንድስ እአአ የካቲት 17/2024
በተፈጠረው ግጭት በርካታ የፖሊስ መኪኖችና አንድ አውቶብስ በእሳት ጋይቷል፤ ሄግ፣ ኔዘርላንድስ እአአ የካቲት 17/2024

በሄግ፤ ኔዘርላንድ፣ በሁለት ተቀናቃኝ ኤርትራውያን ቡድኖች መካከል ቅዳሜ ምሽት በተፈጠረ ግጭት በርካታ የፖሊስ መኪኖችና አንድ አውቶብስ በእሳት ጋይቷል ሲል የከተማዋ ፖሊስ አስታውቋል።

“የኤርትራ መንግስት ታማኝ ደጋፊዎች ስብሰባ በሚያደርጉበት ወቅት፣ መንግስትን የሚቃወሙ ቡድኖች በሥፍራው በመድረስ ጥቃት ፈጽመዋል” ሲሉ የሄግ ማዘጋጃ ቤት ቃል አቀባይ የሆኑት ሮቢን ሚዴል መናገራቸውን የአሶስዬትድ ፕረስ ዘገባ አመልክቷል።

ድንጋይ በመወርወር ላይ የነበሩትን፣ ፖሊስ በአስለቃሽ ጋዝ ለመበተን መሞከሩም ታውቋል።

የፖሊስ ቃል አቀባይ የሆኑት ክርስቲያን ቫን ብላንከን በበኩላቸው፣ በግጭቱ የተጎዳ ሰው ስለመኖሩ ወይም በግጭቱ ከተሳተፉት ውስጥ በቁጥጥር ሥር የዋሉ ስለመኖራቸው በወቅቱ መናገር እንዳልቻሉ ገልጸዋል።

በሄግ የተፈጠረው ግጭት፣ በአውሮፓ ከተስተዋሉት ተደጋግጋሚ ግጭቶች አዲሱ መሆኑ ነው። ባለፈው መስከረም በኤርትራ መንግስት ደጋፊዎች እና ተቃዋሚዎች መካከል ስቱትጋርት፤ ጀርመን፣ ውስጥ በተከሰተ ግጭት 26 የፖሊስ አባላት እንደተጎዱ በወቅቱ ተዘግቦ ነበር። በምዕራባዊ ጀርመን በምትገኘው ጊሰን ከተማ በተፈጠረ ግጭት ደግሞ 22 ፖሊሶች ተጎድተው ነበር።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG