የቆይታ ጊዜው ከአንድ ወር በኋላ የሚጠናቀቀው የአስቸኳይ ጊዜ ዓዋጅ በከፊል ሊራዘም እንደሚችል ጠ/ሚ ኃይለማሪያም ደሳለኝ አስታወቁ፡፡
በዓዋጁ የተጠቀሱ አብዛኛዎቹ ክልከላዎች፣ ትናንትና ተነስተዋል፡፡ የሀገሪቱ የፀጥታ አካላት በአንድ ዕዝ ተቀናጅተው እንዲሰሩ የሚጠይቁ ክስተቶች ግን መሉ በሙሉ አልተወገዱም ብለዋል - ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡
በበተደረገው የሕዝብ አስተያያት ጥናት፣ በጥናቱ ከተሳተፉት ሰማኒያ ሁለት ከመቶው የአስቸኳይ ጊዜ ዓዋጅ "መሉ በሙሉ ወይንም በከፊል እንዲቀጥል" የሚል አስተያየት እንዳለው መረጋገጡን ነው ጠ/ሚኒስትሩ ለፓርላማ አባላት የገለፁት፡፡ አንዳንድ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችም በጠ/ሚኒስትሩ ማብራሪያ ላይ የየራሳቸውን አስተያየት ሰጥተዋል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
በሌላም በኩል ከኤርትራ በየቀኑ ሁለት መቶ የሚሆን ሰው ወደ ኢትዮጵያ እንደሚሰደድና ከመካከላቸውም አምስት ከመቶ የሚሆኑት የሃገሪቱ ወታደሮች የነበሩ መሆናቸውን የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዛሬ እንደገለፁበት ዓይነት ቀደም ሲል ከኢትዮጵያ ለተሰማ መግለጫ የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ የማነ ገብረመስቀል ሰጥተውት በነበረ ምላሽ ለኤርትራዊያኑ መውጣት ሰበቡ “ኢትዮጵያ ነች” ብለዋል፡፡
“ኤርትራ ውስጥ የፖለቲካ ማሳደድ የለም” ያሉት የሃገሪቱ የማስታወቂያ ሚኒስትር ሰዎች የሚወጡት ጨቋኝ መንግሥት ስላለ፣ ወይም በተሣሣቱ የምጣኔ-ኃብት ፖሊሲዎች፣ ወይም ለኑሮ የማይመች ሁኔታ በመኖሩ ሳይሆን “በጦርነትና ከኢትዮጵያ በሚመጣው የጦርነት ሥጋት ምክንያት ነው” ብለዋል፡፡
በመሆኑም ለኢትዮጵያ ግዙፍ ድጋፍ ይሰጣሉ ያሏቸው የአውሮፓ መንግሥታት ጫናቸውን “ኢትዮጵያ ሰላም እንድትሠጠን ለማድረግ ማሳደር አለባቸው፤ እንደ ሕዝብ፣ እንደሃገር በሰላም የመኖር መብት አለን” ብለው ነበር፡፡
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ