“ማንም ኢትዮጵያን መድፈር ሲፈልግ አሥሬ ማሰብ ይኖርበታል” ሲሉ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ አስጠንቅቀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ትላንት "የሉዓላዊነት ቀን" በሚል በአዲስ አበባ በተዘጋጀ መርሃ-ግብር ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር፣ የየትኛውንም ሀገር ስም ባይጠቅሱም “ኢትዮጵያ ከአንዳንድ አገሮች ጋር ግጭት ልትገባ እንደምትችል የሚነገሩ ንግግሮች አሉ” ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ የግጭት ፍላጎት እንደሌላት ጠቅሰው፣ “የሚፈልገንና የሚነካን ካለ ግን አሳፍረን እንመልሳለን” ሲሉ አሳስበዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት፣ ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ ጋር የተፈራረመችውን የመግባቢያ ስምምነት ተከትሎ፣ ከሶማሊያ ጋር ያለው ዲፕሎማሲያዊ ውዝግብ በቀጠለበት ወቅት ነው፡፡
መድረክ / ፎረም