አዲስ አበባ —
ኢትዮጵያ እና ቱርክ በውሃ ልማትና በመከላከያ ዘርፎች ስምምነት መፈራረማቸውን የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት ይፋ አደረገ። ስምምነቶቹ የሁለቱን ሃገሮች ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ከፍ አድርጎታል ተብሏል።
“የኢትዮጵያ መንግሥት በአሸባሪነት በፈረጀው የህወሓት ቡድን ድርጊቶች የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ያሳየው አቋም ፤ ከሁለቱ ሃገሮች ጠንካራ እና ለአያሌ ዓመታት ከኖረ ግንኙነት አኳያ የማይመጥን ነው” ሲሉ የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለአሜሪካው ልዩ ልዑክ አስታወቁ።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡