በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዐብይ አሕመድ አንድ ዓመት


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ

የጠቅላይ ሚኒስትር የአንድ ዓመት የሥልጣን ዘመን የታሰበበት መድረክ አዲስ አበባ፤ ሚሌኒየም አዳራሽ ውስጥ ተካሂዷል።

በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ስላለፈው ዓመትና ስለመጭውም ጊዜ ለግማሽ ሰዓት ያህል የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ንግግራቸውን የጀመሩት ወደ ሥልጣኑ ከዘለቁ አንስቶ ስለተሰጣቸው ድጋፍ በሃገር ውስጥም በውጭም ላሉ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ-ኢትዮጵያ ሁሉ ምሥጋና በማቅረብ ነበር።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ ኢትዮጵያና ስለኢትዮጵያዊነት፣ ስለለውጡና ስለአመጣጡ፣ በዓመቱ ውስጥ ስላጋጠሟቸው ፈተናዎች፣ በንግድና ምጣኔ ኃብት ደረጃ ስለተደረጉ ክንውኖች፣ ስለመጭው ምርጫም ተናግረዋል።

ዶ/ር አብይ አክለውም ስለተፈጠሩ ችግሮች ይቅርታ ጠይቀዋል፣ በመጭው ጊዜ ስለሚያከናውኗቸው ተግባራትም ቃል ገብተዋል፤ ሰላም እንዲሰፍንም ተማፅነዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የዐብይ አሕመድ አንድ ዓመት
please wait

No media source currently available

0:00 0:20:26 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG