“.. ዲሞክራሲያዊ ምርጫ በሌለበት የማገልገል ፍላጎት የለንም። .. በግድ ማስተዳደር ምን እንደሚመስል ግን አይተናል።..” ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ።
“.. ደጋግመን ከዜሮ ጀመርን። ..” ዶ/ር ዮሃንስ ዘለቀ ከአስተናባሪዎች አንዱ።
ባለፈው ሃሙስ ወዲህ ወደ ዋሽንገተን ዲሲ ብቅ ብለው ልዩ ልዩ የምክክር መድረኮችን ያስተናገዱት የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አሕመድ የዩናይትድ ስቴትስ ጉብኝታቸውን አጠናቀው በትላንትናው ዕለት ወደ አዲስ አበባ ተመልሰዋል።
ጠቅላይ ሚንስትሩ በየከተሞቹ የሚኖረውን ኢትዮጵያዊ ብዛትና ከተለያዩ አካባቢዎች ለሚመጡ ብዙዎች ባላቸው አመችነት የተመረጡ በሚመስሉት ሦሥቱ የዩናይትድ ስቴትስ ከተሞች ከተገኙባቸው ልዩ ልዩ መድረኮች የአንዱን ክንውን፤ ከምሁራንና ከቢዝነስ የማሕበረሰብ አባላት ጋር የተካሄደ ውይይት እንመለከታለን።
ታሪክ፣ የመንግስት አስተዳደር እና የዘመን ቅርሶች፤ የቀደሙ አሠራሮችና የአዲሶቹ ንጽጽር ገና ከመግቢያው ከተሰሙት ድምጾች ውስጥ ናቸው።
የጥላቻና የልዩነትን አጥር አፍርሶ በምትኩ ድልድይ መገንባት በሚለው መርሃቸው የስድስት ቀናት የዩናይትድ ስቴትስ ቆይታቸውን አገባደው የተመለሱት ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ቁጥራቸው ከሁለት መቶ ሃምሳ ካልበለጠ ምሁራንና የቢዝነስ ማሕበረሰብ አባላት ጋር ባደረጉት ውይይት በመድረኩ በተናጋሪዎች ለቀረቡ ጥያቄዎች መልስ ሰጥተዋል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ