አዲስ አበባ —
በደቡብ ኢትዮጵያ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ውስጥ በሚገኙ ሦስት ከተሞች ውስጥ ባለፉት አምስት ቀናት በተካሄዱ ግጭቶች 15 ሰዎች መገደላቸውን የክልሉ መንግሥት አስታውቋል።
ግጭቶቹ የተካሄዱት በወልቂጤ፣ ሃዋሣና ወላይታ ሶዶ ከተሞች ውስጥ ሲሆን በክልሉ ውስጥና በአዋሣኝ አካባቢዎች እየተከሰቱ ስላሉ ግጭቶች ከሕዝብ ጋር ለመምከርና መፍትኄ ለመሻት በመጭው ሣምንት ወደዚያው እንደሚሄዱ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ አስታውቀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ ላይ ያደረጉትን የአንድ ቀን ጉብኝት አጠናቅቀው አዲስ አበባ ሲገቡ ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃል “ከእርስ በርስ ግጭት የሚያተርፉት የፖለቲካ ነጋዴዎች ናቸው” ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትናንት /ዓርብ/ ተመሣሣይ ንግግር አድርገዋል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ