ዋሺንግተን ዲሲ —
ፕሬዚዳንቱ ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር በሁለትዮሽና በአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸውን የሃገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
የፕሬዚዳንት ሞሐመድ ዐብዱላሂ ጉብኝት - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በአፍሪካ ቀንድ ሰላም ለማስፈንና የኢኮኖሚ ትስስርን ለማጠናከር የጀመሩት ዲፕሎማሲያዊ እንቅሰቃሴ አካል ነው ተብሏል።