በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“መንግሥትን ከ“ሸኔ” ጋራ የሚያደራድር ኮሚቴ ተቋቁሞ እየሠራ ነው፤” - ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ


“መንግሥትን ከ“ሸኔ” ጋራ የሚያደራድር ኮሚቴ ተቋቁሞ እየሠራ ነው፤” - ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:59 0:00

“መንግሥትን ከ“ሸኔ” ጋራ የሚያደራድር ኮሚቴ ተቋቁሞ እየሠራ ነው፤” - ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

“ወደ እኛ የመጣ የሰላም ድርድር ጥያቄ የለም” የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ቃለ አቀባይ

የኢትዮጵያ መንግሥት፣ በአሸባሪነት ከፈረጀውና “ሸኔ” ብሎ ከሚጠራው ታጣቂ ቡድን ጋራ፣ ለሰላም የሚያደራድረውን በብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት የሚመራ ኮሚቴ አቋቁሞ እየሠራ መኾኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ።

ራሱን፥ “የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት” ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ብድን ዓለም አቀፍ ቃል አቀባይ ኦዳ ተርቢ ከቨርጂኒያ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል፤ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ቃል አጣጥለው፣ ወደ እነርሱ የመጣ የሰላም ድርድር ጥያቄ እንደሌለ ገልጸዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ግን፣ የታጣቂዎቹን አመራሮች በተናጠል ሲያነጋግሩ መቆየታቸውን ጠቁመዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ ዛሬ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደራሴዎች ለተነሣላቸው ጥያቄ ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት፣ መንግሥት ከታጣቂ ቡድኑ ጋራ ለመነጋገር ውሳኔ አሳልፎ፣ “ባለፉት ኹለት ወራት ገደማ ከ10 በላይ ሙከራ አድርጓል፤” ብለዋል፡፡ ይኹን እንጂ፣ ቡድኑ በአንድ ጥላ ሥር የተደራጀ ባለመኾኑ፣ እስከ አሁን ውጤት እንዳልተገኘ ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል ፓርላማው፣ ህወሓት ከሽብርተኝነት ዝርዝር ውስጥ እንዲነሳ በመወሰኑ ምስጋና ያቀረቡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ከዚኽ ጋራ በተያያዘ፣ ከምክር ቤቱ አባላት የሚነሡ ሥጋቶች በቀጣይ በውይይት እንደሚፈቱ አመላክተዋል።

በኢትዮጵያ ያለው የሰላም መደፍረስ መቀጠሉንና ዜጎች በነፃነት መንቀሳቀስ አለመቻላቸውን በመጥቀስ፣ “ሥልጣንዎን በመልቀቅ እና ተጠያቂ በመኾን የመፍትሔው አካል ለመኾን አላሰቡም ወይ?” በሚል ለተነሣላቸው ጥያቄም ምላሽ ሰጥተዋል።

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG