በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አብይ አሕመድ ሞቃዲሾ ነበሩ

የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሞሐመድ አብዱላሂ /ፎርማጆ/ የኢትዮጵያን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድን ሞቃዲሾ አደን አብዱሌ አይሮፕላን ጣቢያ ተገኝተው በተቀበሉበት ወቅት፤ /ቅዳሜ፤ ሰኔ 9/2010 ዓ.ም/
የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሞሐመድ አብዱላሂ /ፎርማጆ/ የኢትዮጵያን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድን ሞቃዲሾ አደን አብዱሌ አይሮፕላን ጣቢያ ተገኝተው በተቀበሉበት ወቅት፤ /ቅዳሜ፤ ሰኔ 9/2010 ዓ.ም/

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድና የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሞሐመድ አብዱላሂ /ፎርማጆ/ በሁለቱ ሃገሮቻቸው መካከል ያሉትን ወንድማዊ ግንኙነቶች ለማጠናከር ዛሬ ተስማምተዋል።

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድና የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሞሐመድ አብዱላሂ /ፎርማጆ/ በሁለቱ ሃገሮቻቸው መካከል ያሉትን ወንድማዊ ግንኙነቶች ለማጠናከር ዛሬ ተስማምተዋል።

የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሞሐመድ አብዱላሂ /ፎርማጆ/ና የኢትዮጵያን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ /ሞቃዲሾ ፤ ቅዳሜ፤ ሰኔ 9/2010 ዓ.ም/
የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሞሐመድ አብዱላሂ /ፎርማጆ/ና የኢትዮጵያን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ /ሞቃዲሾ ፤ ቅዳሜ፤ ሰኔ 9/2010 ዓ.ም/

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ለአንድ ቀን ጉብኝት ዛሬ /ቅዳሜ፤ ሰኔ 9/2010 ዓ.ም./ ሞቃዲሾ አደን አብዱሌ አይሮፕላን ጣቢያ ሲደርሱ ፕሬዚዳንት ሞሐመድ /ፎርማጆ/ እዚያው ተገኝተው የተቀበሏቸው ሲሆን ሁለቱ መሪዎች ቆንስላዎችንና የንግድ ቢሮዎችን ሁለቱም ሃገሮች ውስጥ መክፈትን ጨምሮ ዲፕሎማሲያዊና የንግድ ግንኙነቶቻቸውን ለማጠናከር፣ እንዲሆም በምጣኔ ኃብቶቻቸው መስፋፋት ላይ ጫኖ ሊያሳድሩ የሚችሉ ሁሉንም መሰናክሎች ለማንሳት ወስነዋል።

የሁለቱ መሪዎች ዋነኛ ትኩረት የምጣኔ ኃብት ዕድገትና የሁለቱንም ሃገሮች መዋዕለ ነዋይ ማስፋት ቢሆንም በማንኛውም ገፅታ የሚከሰት ሽብር ፈጠራን አውግዘው ሽብርተኝነትንና ድንበር ዘለል የፀጥታ ችግሮችን በጋራ ለመጋፈጥ ተስማምተዋል።

በዶ/ር አብይ አሕመድ ደረጃ ያለ የኢትዮጵያ መሪ ሶማሊያን ለመጨረሻ ጊዜ የጎበኘው የዛሬ አሥራ አንድ ዓመት ሶማሊያን ለጥቂት ወራት ተቆጣጥሮ ያስተዳደረውን የእሥላማዊ ችሎቶች መንግሥት ከሥልጣን ለማባረር ኢትዮጵያ ቁልፍ ሚና ከተጫወተች በኋላ ወደዚያው የሄዱት የወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ነበሩ።

የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዛሬ ሞቃዲሾ ሲገቡ የፀጥታ ጥበቃው እጅግ የተጠናከረ እንደነበርና መንገዶች ሁሉ መዘጋቸው ተዘግቧል።

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ኅብረቱ የሶማሊያ የሰላም ጥበቃ ኃይል - አሚሶም ውስጥ አራት ሺህ ሁለት መቶ ወታደሮቿን አሠማርታለች።

አብይ አሕመድ በሞቃዲሾ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:35 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG