በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሥልጣን በኢትዮጵያ የዕድሜ ልክ አይሆንም


ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ /ፎቶ ፋይል/
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ /ፎቶ ፋይል/

የኢትዮጵያ መሪዎች የሥልጣን ጊዜ ከሁለት የምርጫ ዘመን እንዳይበልጥ ሕገመንግሥታዊ ገደብ እንደሚጣል ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ አስታወቁ።

የኢትዮጵያ መሪዎች የሥልጣን ጊዜ ከሁለት የምርጫ ዘመን እንዳይበልጥ ሕገመንግሥታዊ ገደብ እንደሚጣል ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ አስታውቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በደቡብ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ዋና ከተማ ሃዋሣ ዛሬ ተገኝተው ከነዋሪዎቿ ጋር በተወያዩበት ወቅት “ኢትዮጵያ በማደግ ላይ ያለች ሃገር በመሆኗ ጥቂት ሰዎችን ለረዥም ጊዜ ሥልጣን ላይ ማቆየት አትችልም” ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም ማንም የኢትዮጵያ መሪ ከአሁን በኋላ ከሁለት የሥልጣን ዘመናት በላይ ማገልገል የማይችል ስለመሆኑ ሕገ መንግሥታዊ ማሠሪያ እንደሚደረግለት ተናግረዋል።

“የዕድሜ ልክ ሥልጣን ኢትዮጵያ ውስጥ ያበቃ መሆኑን አሁን ላለነው፤ ለሚመጡትም ለማስተማር ጭምር መሆኑን ግንዛቤ ቢወሰድ ጥሩ ነው” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ሥልጣን በኢትዮጵያ የዕድሜ ልክ አይሆንም
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:09 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG