በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጠ/ሚኒስትር ዐቢይ ማብራሪያ - ለአፍሪካ ህብረት


ፎቶ ፋይል፦ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ
ፎቶ ፋይል፦ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ

ሀገራቸው "በተመሳጠረ ዓለም አቀፍ የትችት ማዕበል ውስጥ እያለፈች" መሆንዋን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በዚህ ወቅት አፍሪካውያን ለአፍሪካ ችግር አፍሪካዊ መፍትሄን በመደገፍ ከኢትዮጵያ ጎን እንዲቆሙ ጥሪ አቅርበዋል።

ሀገራቸው በዚህ ሁኔታ ውስጥ እያለፈች ያለችውም በገዛ ግዛቷ ውስጥ የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ በመስራቷ መሆኑንም ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የገለጹት።

የአፍሪካ ህብረት በትግራይ ክልል ደረሱ የሚባሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮምሽን ጋር ሆኖ እንዲያጣራ ፈቃደኛ መሆናቸውንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ይህን ገለጻ ያደረጉት በዝግ ለተካሄደው የአፍሪካ ህብረት የሰላም እና ጸጥታ ምክር ቤት ስብሰባ ነው። ሰፋ ያለውን ዘገባ በነገ ፕሮግራም እናቀርባለን።

XS
SM
MD
LG